Get Mystery Box with random crypto!

በነገው ዕለት ጠዋት 2:30 ላይ የኢድ ሰላት እንደሚሰገድ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ | Fast mereja

በነገው ዕለት ጠዋት 2:30 ላይ የኢድ ሰላት እንደሚሰገድ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ። ህዝበ ሙስሊሙም ይህንን አውቆ ሰዓቱን ጠብቆ በቦታው እንዲገኝ ተብሏል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለህዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

የ1444ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል አስመልክቶ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።

ህዝበ ሙስሊሙ በእድሳት ላይ በሚገኘው እስታዲየም የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል ሰላት እንዲሰግድ ከሚመለከተው አካል ጋር ማመቻቸት መቻሉ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ህዝበ ሙስሊሙ ሰላሙን አስጠብቆ በአንድነት፣ የተቸገሩ ወገኖች በመርዳት በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ ቀርቧል።

JEILU TV