Get Mystery Box with random crypto!

Feta Daily

የቴሌግራም ቻናል አርማ fetadaily_news — Feta Daily F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fetadaily_news — Feta Daily
የሰርጥ አድራሻ: @fetadaily_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.13K
የሰርጥ መግለጫ

Fetadaily.com
Media and News website
ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው!

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-22 15:55:17
በሱዳን የሚገኙ የውጭ ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው ሊወጡ ነው

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (RSF) 'ወዳጅ' ሲል የገለጻቸው ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን እንዲያስወጡ ለማስቻል ሁሉንም የሱዳን አየር ማረፊያዎችን ለመክፈት መዘጋጀቱን ገለጸ።

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሀገራት ዜጎችን የማስወጣት ሂደቱን እንደሚያስተባብር ማስታወቁን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል።

በተያያዘ መረጃ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የፈረንሳይና የቻይና ዲፕሎማቶች እና ዜጎች በወታደራዊ አውሮፕላኖች ከካርቱም እንዲወጡ ሊደረግ መሆኑን የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን የውጭ አገር ዜጎቹ “በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ” የሚወጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እና ለማስተባበር መስማማታቸውን መግለጫው ጠቅሷል።
420 views🅐🅑🅓🅨, 12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 14:11:32 1) ለጀኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ቦሌ ሩዋንዳ የቆመው ሐውልትና ፓርክ ዛሬ በይፋ ተመርቋል። ሐውልቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው በይፋ የተመረቀው። የቀድሞ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን “ሰራዊት ሀገር እንጂ ብሄር የለውም!” በሚል እምነት እና አስተሳሰባቸው ይታወቁ እንደነበር በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

2) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ዒድ እና ዳግም ትንሣኤን ያጣመረ የተፈናቃዮች ምገባ ተካሄዷል። ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ከ20ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች፣ የዒድ አልፈጥርንና የዳግም ትንሣኤን በዓላት ምክንያት በማድረግ የምገባ ሥርዐት መከናወኑን፣ የዞኑ የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታወቋል፡፡

3) በወላይታ ዞን በተካሔደው 'ውሳኔ ሕዝብ' የምርጫ ዐዋጅ ጥሰት ፈጽመዋል፤ የተባሉ 93 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡ ወንጀሉን ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው የሚፈለጉት 136 ሲኾኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ 18ቱ፥ በልዩ ልዩ ደረጃዎች የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ሲሆኑ፤ 118ቱ ደግሞ፥ የምርጫ አስፈጻሚዎች እንደኾኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመልክቷል።

4) ሳምንት የደፈነው የሱዳን ጦርነት ተፋፍሞ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ የውጭ አገራት ዜጎቻቸውን ከመዲናዋ ካርቱም ለማስወጣት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ ዜጎቹን ከካርቱም ለማስወጣት እቅድ መንደፉን አስታውቋል። በአንፃሩ አሜሪካ የዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ካርቱምን ለቀው እንዲወጡ ለማድረግ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰች ገልጻለች። ባለስልጣናቱ ከኤምባሲው ሰራተኞች ውጭ ያሉ ሌሎች የአሜሪካ ዜጎች ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በራሳቸው እንዲዘጋጁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

5) በደቡብ አፍሪካ ቤታቸው ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው የአንድ ቤተሰብ 10 አባላት መገደላቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጿል። ደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ቁጥር ግድያ ከሚፈጸምባቸው ሀገራት አንዷ እንደሆነች መረጃዎች ያመለክታሉ። ጥቃቱ በተፈጸመበት ስፍራ አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች የተኩስ ድምጽ መስማታቸውን ተከትሎ ለፖሊስ በማሳወቃቸው ጉዳዩ ተደርሶበታል። የፖሊስ ሚኒስትሩ ከጥቃቱ ሰለባዎች መካከል የ13 ዓመት ልጅ እንደሚገኝ ገልጸው ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ የሚያሳቅቅ መሆኑን አመልክተዋል።
ቴሌግራም : https://t.me/world_info1
462 views🅐🅑🅓🅨, 11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 11:13:40 1) አማራ ክልል፤ ለተፈናቃዮች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ እንደከበደው ገልጿል። በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ የተፈናቀሉ 300 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም ከወለጋ፣ ከመተከልና ከወልቃይት የተፈናቀሉ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በክልሉ ከ700 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ መረጃው አመላክቷል።

2) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በዛሬው የዒድ ክብረ በዓል ላይ ሕዝበ ሙስሊሙ፣ በክልሉ መልሶ ግንባታ ሒደት ላይ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡ የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ አደም ዓብደልቃድር ጁሃር በበኩላቸው፣ "የዘንድሮ ዒድ አልፈጥር በዓል፣ ካለፉት ዓመታት በተሻለ ሰላም እና ተስፋ መከበሩን ገልፀዋል።

3) የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታቸው ወጥተው የሰላት ሥነ ስርዓቱ ላመለጣቸው የአዲስ አበባ ከተማ እና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ፤ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠይቋል። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣ በደስታ በመጠናቀቁ መደሰቱን በመግለጽ፤ የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰዓት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣቸው የከተማዋ ሙስሊም ማህበረሰቦች ይቅርታ ጠይቋል።

4) በሱዳን ለኢድ የታሰበው ተኩስ ማቆም ከሽፎ ውጊያው መቀጠሉ ተመላክቷል። በሱዳን የሁለቱ ተቀናቃኝ ጄኔራሎች ወታደሮች ዛሬ ዓርብ በካርቱም ጎዳናዎች ላይ ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ ውለዋል። ዛሬ ተከብሮ የዋለውን የኢድ በዓል ምክንያት በማድረግ የተኩስ ስምምነት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፣ ሳይከበር ቀርቷል። በሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን እና በአር.ኤስ.ኤፍ መሪ ጀነራል ሞሃመድ አምዳን ደጋሎ ወይም ሄመቲ ወታደሮች መካከል ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ፣ በተለይም በመዲናዋ ካርቱምና በሌሎችም ከተሞች በተደረገው ውጊያ፣ ከ400 በለይ ሰዎች ሲሞቱ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተጎድተዋል።

5) ዩክሬን በመጨረሻ ኔቶን እንደምትቀላቀል የኔቶ ዋና ጸኃፊ ገልፀዋል። የህብረቱ ዋና ፀሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ''ሁሉም የኔቶ አጋሮች ዩክሬን የህብረቱ አባል እንድትሆን መስማማታቸውን አንስተው፤ ዋናው ትኩረት ሀገሪቱ በሩሲያ ላይ የበላይነትን እንድትቀዳጅ ማብቃት መሆኑን አመላክተዋል። በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ስጋት የገባቸው ስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበው፣ ፊንላንድ ወታደራዊ ጥምረቱን መቀላቀሏ ይታወሳል።
487 views🅐🅑🅓🅨, 08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 11:13:40 1) ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ጦር ከሱዳን ጋር ተጋጭቷል መባሉ ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት በሁለቱ አገራት አዋሳኝ ድንበር ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ በሱዳን ኃይሎች ላይ ጥቃት ከፍቷል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአረብኛ ባወጡት መግለጫ ላይ ይህን አይነት ሐሰተኛ ሪፖርቶችን የሚያሰራጩ ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

2) በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች የሚበላ የሚጠጣ ከማጣታቸዉም በላይ ምንም አይነት መረጃን እንደማያገኙ ተናግረዋል። በታጣቂ ሚሊሺያዎች ንብረታችን እየተዘረፈ ነዉ ያሉት ዜጎች ከሁሉ በላይ ግን እያስጨነቀን ያለዉ ቤታችን ቁጭ ብለን በተባራሪ ጥይት አልያም የአዉሮፕላን ጥቃት ሰለባ እንዳንሆን ነዉ ማለታቸው ተሰምቷል።

3) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው የሰላም ልኡክ በቀጣይ ሳምንታት ወደ ትግራይ ክልል ሊጓዝ መሆኑ ተገልጿል። የሰላም ልዑኩ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡን አስትውሷል። በትግራይ ክልል የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ከልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ መቆየታቸውንም ገልጿል። ልኡኩ የደብዳቤው ግንኙነት እንደታሰበው የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አመልክቷል። ልኡኩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ክልል ትግራይ በመጓዝ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን በመግለጫው አረጋግጧል።

4) የሲዳማ የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ ክብረ በዓል፥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በኾነችው በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሶሮሳ ጉዱማሌ ሰንጎ ተከብሯል። የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት የሚያከብር ሲሆን፤ በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል። ይህ በዓል መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል።

5)የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ፣ ከ2013 ዓ.ም. ሰኔ ወር በኋላ፣ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ መክፈል መጀመሩን፣ የክልሉ የፋይናንስ እና የሀብት ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጿል፡፡ የደመወዝ ክፍያው፣ የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የላከውን በጀት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ ለመንግሥት ሠራተኞች የሦስት ወራት ደመወዛቸውን በመክፈል መጀመሩን መረጃው አመላክቷል።
473 views🅐🅑🅓🅨, 08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:19:36 1) ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ጦር ከሱዳን ጋር ተጋጭቷል መባሉ ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት በሁለቱ አገራት አዋሳኝ ድንበር ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ በሱዳን ኃይሎች ላይ ጥቃት ከፍቷል የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአረብኛ ባወጡት መግለጫ ላይ ይህን አይነት ሐሰተኛ ሪፖርቶችን የሚያሰራጩ ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

2) በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች የሚበላ የሚጠጣ ከማጣታቸዉም በላይ ምንም አይነት መረጃን እንደማያገኙ ተናግረዋል። በታጣቂ ሚሊሺያዎች ንብረታችን እየተዘረፈ ነዉ ያሉት ዜጎች ከሁሉ በላይ ግን እያስጨነቀን ያለዉ ቤታችን ቁጭ ብለን በተባራሪ ጥይት አልያም የአዉሮፕላን ጥቃት ሰለባ እንዳንሆን ነዉ ማለታቸው ተሰምቷል።

3) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው የሰላም ልኡክ በቀጣይ ሳምንታት ወደ ትግራይ ክልል ሊጓዝ መሆኑ ተገልጿል።  የሰላም ልዑኩ  በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡን አስትውሷል። በትግራይ ክልል የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ከልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ መቆየታቸውንም ገልጿል። ልኡኩ የደብዳቤው ግንኙነት እንደታሰበው የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አመልክቷል። ልኡኩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ክልል ትግራይ በመጓዝ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን በመግለጫው  አረጋግጧል።

4) የሲዳማ የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ ክብረ በዓል፥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫ በኾነችው በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሶሮሳ ጉዱማሌ ሰንጎ ተከብሯል። የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት የሚያከብር ሲሆን፤ በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል። ይህ በዓል መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል።

5)የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ፣ ከ2013 ዓ.ም. ሰኔ ወር በኋላ፣ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ መክፈል መጀመሩን፣ የክልሉ የፋይናንስ እና የሀብት ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጿል፡፡ የደመወዝ ክፍያው፣ የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የላከውን በጀት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ ለመንግሥት ሠራተኞች የሦስት ወራት ደመወዛቸውን በመክፈል መጀመሩን መረጃው አመላክቷል።

ቴሌግራም : https://t.me/world_info1
770 views🅐🅑🅓🅨, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 09:13:55
#ዒድ_አልፈጥር

ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩ ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
መልካም በዓል !

ፎቶ፦ አቤል ጋሻው (ፋይል)

ቴሌግራም : https://t.me/world_info1
743 views🅐🅑🅓🅨, 06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:13:00
እንኳን ለ 1444ኛው የኢድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ የሸዋል ወር ጨረቃ በሌሎች ሃገራት እና በሳኡዲ አረበያ በመታየቷ የታላቁ
የረመዳን ፆም በዛሬው እለት ሀሙስ ሚያዚያ 12 መጠናቀቁ ታውቋል፡፡ የኢድ አል ፊጥር በዓል በነገው ዕለት አርብ ሚያዚያ 13 መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኢድ ሙባረክ!
1.0K views🅐🅑🅓🅨, 16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:00:44 1)  ዒድ አልፈጥር ዛሬ ማታ ጨረቃ ከታየች ነገ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል። የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት፤ የ2015 የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ማታ ከታየች ነገ፣ ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ እንደሚከበር አስታውቋል። የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት የ2015 የዒድ አልፈጥር በዓል አከባበርን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመግለጫውም 1 ሺሕ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ሕብረተሰብ  የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን አስተላልፏል። ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ  ሙስሊሙ ሕብረተሰብ  በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ ማቅረቡ ተገልጿል።

2)   መንግሥት በሱዳን ባለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናው መስሪያ ቤት እና ካርቱም በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ አማካኝነት የኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ለመጠበቅ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡ የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና አጎራባች ክልሎች አባል የሆኑበት ግብረ ኃይል በሀገር አቀፍ ደረጃ መቋቋሙም ተመላክቷል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስፈላጊ መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ አመላክቷል።

3)  የጉሙሩክ ኮሚሽን በኮንትሮ ባንድ ንግድ ላይ የጸጥታ አካላት እጃቸው የረዘመ በመሆኑ የኮትሮ ባንድ ንግድ መቀነስ አልተቻለም ሲል አስታወቋል፡፡ በፀጥታ አካላት የሚደግፉት የኮንትሮባንድ አሳላፊዎችና ነጋዴዎች ቁጥራቸው እየተበራከተ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ ባለፉት ስምንት ወራቶች ውስጥ ሁለት ኮኖኔሎች እና ሌሎችም የክልል የጸጥታ አካላት በኮንትሮባንድ ንግድ ተሳትፈው መያዛቸው ተገልጿል፡፡ ኮሚሽኑ በተያዘው በበጀት አመቱ ስምንት ወራቶች ውስጥ 5 ቢሊዮን ብር ከኮንትሮ ባንድ ንግድ ማዳን እንደተቻለ ገልጿል።

4)  የሱዳን ቀውስ በጎረቤት አገራት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ እንደሆነ ምሁራን አመላክተዋል። ምሁራኑ ‘’የቀይ ባህር መስመር የዓለም መሠረታዊ የንግድ መስመር እንደመሆኑ፤ ሱዳንም ትልቅ ሃገር ከመሆኗ አንጻር ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ ግጭት መፈጠሩ ለቀጠናው ከፍተኛ የሆነ ስጋት እንደሚፈጥር ጠቁመዋል። በተለይ በኢትዮጵያ የሚኖረው ተፅዕኖ የጎላ ሊሆን እንደሚችል አመላክተው፤ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘና ሁለቱ አገራት በድንበር ከመተሳሰራቸውም በላይ፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሱዳን ውስጥ መኖራቸው፤ የሀገራቱን ትስስሮሽ የጠነከረ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

5)  ሩሲያ ሰሜን ኮሪያን ልታስታጥቅ እንደምትችል አስጠንቅቃለች። አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ላይ መሆናቸው ይታወሳል። አሜሪካ ወዳጅ የምትላቸውን ሀገራት በማግባባት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዲለግሱ በማድረግ ላይ ስትሆን፤ በዚህም ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንድትሰጥ ማግባባቷ ተገልጿል። ደቡብ ኮሪያም ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ለመስጠት ሁኔታዎችን እየገመገመች መሆኑን ከሰሞኑ አስታውቃለች። ሩሲያ ባወጣችው መግለጫ ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳትሰጥ አስጠንቅቃ፤ ደቡብ ኮሪያ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ ችላ ብላ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ከሰጠች፤ ሩሲያ በአፀፋው ለሰሜን ኮሪያ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እንደምታስታጥቅ ገልጻለች።

ቴሌግራም : https://t.me/world_info1
893 views🅐🅑🅓🅨, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 14:21:44

734 views🅐🅑🅓🅨, 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 12:45:42 1) በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሠላም ስምምነትና ያንን ተከትሎም የሚታየውን አሉታዊ ለውጥ በበጉ እንደሚቀበሉት በጃፓን በስብሰባ ላይ የሚገኙት የቡድን 7 የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ የቡድን 7 የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ የአፍሪካ ሕብረት በሠላም ስምምነቱ ላይ የተጫወተውን ሚና አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነት እንዲሠፍን የሚደረገው ጥረት እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡ የሠላም ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ በመተግበር ረገድ ሁለቱም ወገኖች ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቆጣጣሪዎች ካለገደብ እንዲቀሳቀሱ እንዲፈቀድ ጠይቀዋል፡፡

2) አቶ አንዷለም አራጌ ከኢዜማ ፓርቲ በይፋ መልቀቃቸውን አሳውቀዋል። በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ከሥመ ገናናዎቹ ጎራ የሚመደቡት፤ አቶ አንዷለም አራጌ ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማን) ከመሠረቱትና ከአመራሮቹ አንዱ ሲሆኑ የፓርቲያቸውን ቁመና «አሰላለፍ» ለማስተካከል ከመሞገትም አልፈው «በአባላት ፊት» ቀርበው ያደረጉት ሙግት ተገቢውን ድጋፍ አለማግኘቱን ጠቅሰዋል።

3) በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክንያት፣ በትግራይ፣ ከሦስት ዓመት በላይ ተስተጓጉሎ የቆየው ትምህርት፣ ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሚጀመር የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቋል፡፡ ተማሪዎች ከትምህርት ርቀው ያሳለፏቸውን ዓመታት ለማካካስ፣ በአንድ ዓመት፤ የሁለት መንፈቅ ዓመት ትምህርት በመሸፈን ለማስተማር መታቀዱንና፤ ይህም በከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደሚፈጸም የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመላክቷል።
4) ጦርነቱ ለስድስተኛ ቀን ተፋፍሞ በቀጠለባት ሱዳን በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከዋና መዲናዋ ካርቱም እየሸሹ ሲሆን የውጭ አገራትም ዜጎቻቸውን ለማስወጣት እየሞከሩ መሆኑ ተገልጿል። ረቡዕ ማለዳ ከፍተኛ ፍንዳታዎች እና የተኩስ እሩምታዎች ከተማዋን እያናወጣት በነበረበት ወቅት በርካቶች በመኪና እንዲሁም በእግራቸው ከተማዋን ለቀው ሲወጡ ተስተውለዋል። የጃፓን እና የታንዛንያ ባለስልጣናት ዜጎቻቸውን ለማስወጣት ዝግጅት መጀመራቸውን ተናግረዋል። በርካቶች ከመዲናዋ መውጣትም የጀመሩት፤ በተፋላሚ ወገኖች ተደርሶ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት መፋረሱን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

5) በየመን ዋና ከተማ ሰንአ በተፈጠረ ትርምስ ከ70 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። በከተማዋ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ የረመዳን ወርን በማስመልከት ሲደረግ የነበረ ድጋፍን ተከትሎ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨናነቀ ሁኔታ ተሰባስበው እንደነበር ዘገባው ጠቁሟል። እርዳታውን ሲያድሉ የነበሩ ሰዎች ታስረው ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ገልጿል።

ቴሌግራም : https://t.me/world_info1
734 views🅐🅑🅓🅨, 09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ