Get Mystery Box with random crypto!

#ትሻገረዋለህ በፊትህ ተደቅኖ አላልፈውም ያልከውን፣ በሃይልህ እና በችሎትህ የማትሻገረውን፣ እንዴ | ፍኖተ ~ ጽድቅ

#ትሻገረዋለህ

በፊትህ ተደቅኖ አላልፈውም ያልከውን፣ በሃይልህ እና በችሎትህ የማትሻገረውን፣ እንዴት ይሆን ብለህ ግራ የተጋባህበትን፣ ጠላት ባሳደድህ ጊዜ ፊትህ የተደቀነብህን፣ በአዕምሮ ልታስበው ታክቶህ ተስፋ ያጣህበትን፣ የአለመቻል ጥጉ ይሄ ነው ያልከውን፣ ከፊትህ ከቆመው መከራ የተነሳ ልክ ያልነበርክበትን ጊዜ ያስናፈቀህን ያንን መከራ እግዚአብሔር ያሻግርሃል። የገጠመህ ምንም ሊሆን ይችላል ከገጠመህ ነገር በላይ ግን የሚያሻግርህን አስበው። በእግዚአብሔር ፊት የቱ ተራራ ደልዳላ ሜዳ አልሆንም ይላል? የትኛም በህር የሱ የሆኑት ያሰምጣል? የትኛም ችግር ፈቺውን ይክዳል? የቱስ መከራ የሱ አቅም ይፈትናል? አንተ አለሁበት የምትለው ፈተና በእግዚአብሔር ፊት ምንም ነውና አሻግሮህ እንደታሪክ እንድትናገረው ያደርግሃል። ከዚህ ነው ያተረፈኝ እያልክ የእግዚአብሔር ድንቅ ስራ ትመስክረበታለህ። እግዚአብሔር አንተን ካለህበት ችግር ለማውጣት ዘወትር መዳፉ የተዘረጋ ነው። ችግሮች አቅማቸውን የሚያጡት ፈቺያቸው እግዚአብሔር ጋር ሲመጡ ነው። ለአንተ ካባድ የመሰለህ ነገር ለአንተ እንጂ ለአባትህ ለእግዚአብሔር ቀላል ነው።

የሀሳብ ምንጭ : ኢየሱ ምዕራፍ 4

ዲያቆን ተስፋ መሠረት
ነሐሴ 6/2014 ዓ.ም

ይቀላቀሉ ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek