Get Mystery Box with random crypto!

#ከመጽሐፍት_አለም ነፍስ አትሞትም። እርሷ ስለ ዘላለም ሕይወት ወይም ስለ ዘላለም ቅጣት ለ | ፍኖተ ~ ጽድቅ

#ከመጽሐፍት_አለም

ነፍስ አትሞትም። እርሷ ስለ ዘላለም ሕይወት ወይም ስለ ዘላለም ቅጣት ለዘላለም ትኖራለች። ነፍስ የሕይወቷ አስገኒ ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር የምትለያይ ከሆነ በቅጣት ትኖራለች። እኛ ነፍሳችንን የምንከብርና ከፍ ከፍ የምናደርጋት ከሆንን ስጋዊ ፍላጎታችንን መተው ቀላል ነገር ነው።

መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እነሆ የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት"(ሉቃ 17:21) ብሎናል። አይሁድ ይሹት የነበረው ምድራዊውን መንግስት ነበር፤ ክርስቶስ በልባችን ውስጥ የገነባው ግን ዘላለማዊ መንግስት ነው። ስለሆነም ንጹህ መሆን ከፈለጋችሁ ውስጣዊው ሰዋችሁን በመመልከት ለነፍሳችሁ ድህነት ጥንቃቄ አድርጉ።

ወደ ልባችሁ ውስጥ ተመልክታችሁ ለውስጣዊው ሰዋችሁ በእውነት የምትታገሉ ከሆናችሁ፤ ሕይወታችሁን በእግዚአብሔር እጆች ላይ የምትጥሉና በልባችሁ ውስጥ ላለው ለመንፈስ ቅዱስ ስራ ምላሽ የምትሰጡ ከሆናችሁ፤ በዓለም ውስጥ እጅግ ደስተኛዎቹ ሰዎች ትሆናላችሁ! ጉዳዩ ይህ ከሆነ በማንኛውም ስጋዊ ምኞት ወይም ርኩሰት ፈጽሞ ልትሸነፉ አትችሉም። ስለዚህ ንጽሕናን በሕይወታችሁ ውስጥ በሚገኙት በሁሉም ሁኔታዎች ላይ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ።



#ርዕስ: ወጣቶችና የንጽሕና ህይወት
#ጸሐፊ፡ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
#ገጽ: 20 እና 21



ይቀላቀሉን ➟ @fenote_tsedek
በቅንነት ያጋሩ ➟ @fenote_tsedek