Get Mystery Box with random crypto!

ሐረር ፈለገ ሕይወት ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ felegeh — ሐረር ፈለገ ሕይወት ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ felegeh — ሐረር ፈለገ ሕይወት ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @felegeh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 359
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል በሐ/መ/ሥላሴ/ካ እና የሸ/ደ/ገ/መ/መ/ቅዱስ ዮሐንስ/ገ /ፈ/ሕ/ሰ/ት/ቤት መማማርያ ይሆን ዘንድ ነው✿✿✿
" በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ"
መክ ፩፪:፩
ለአስተያየቶ
@felegeh-commentbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 20:23:36 ማሳሰቢያ
አመታዊው የደብሩ ስበከተ ወንጌል ከሰንበት ት/ቤቱ በጋር በመሆን የሚያዘገጅት የክረምት ትምህር/ኮርስ የተጀመረ መሆኑን #በሰፈራችን#በትምህርት ቤት#በአካባቢያች ያሉ #ህጻናት#ወጣቶች #ጎልማሶችን እያሳወቃችሁና እየቀሰቀሳችሁ ክረምቱን በበጎ እንዲያሳልፋ የሰ/ት/ቤቱ አባላት የበኩላችሁን ሀላፊነት እንድትወጡ ስንል እናሳስባለን ።
# ከ15 አመት በታች ለሆኑ ጠዋት 12:00-1:30
#ከ15 አመት በላይ ለሆኑ ከምሽቱ 12:00-1:45 ት/ቤት ጊቢ ውስጥ
felegeh
felegeh
felegeh
66 viewsX, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 06:30:52 ክፍል (45)
#ነገረ ድኅነት
#በነገረ ድኅነት የምስጢረ ተዋህዶ #ምሳሌዎች
ሀ /የእሳትና #ብረት ውህደት
(የጋለ ብረት)
#ብረትና እሳት #ሲዋሐዱ ብረቱ ከእሳት በገባ ጊዜ #እሳቱ #የብረቱን ገነዘብ
(ባሕርይ ) ገንዘብ ያደርጋል #ብረቱም የእሳቱን ገንዘብ ያደርጋል ልክ መለኮት የሥጋን ሥጋም የመለኮትን#ገንዘብ ገንዘብ እንዳደረጉት ማለት ነው።
የቃል (መለኮት ) ገንዘብ #የሥጋ ሆነ ።
#የሥጋ ገንዘብም ከኃጢአት በስተቀር የቃል ሆነ
" ሃይ አበው ዘቄርሎስ
#እሳት ረቂቅና ብሩህ ነው ነገር ግን #የብረትን ገንዘብ ገንዘብ በማድረግ በተዋሐዱ ጊዜ
ግዙፍ(የሚያዝ የሚጨበጥ የሚዳሰስ ) ነው።
#እንደዚሁም #ሥጋ በባሕርይው ግዙፍና ውሱን ነው
#መለኮትን በተዋሐደ ጊዜ ግን
#በመለኮት ገንዘብ ረቂቅ ምሉዕ ክቡር ባለጸጋ ነው ።
#መለኮትም በሥጋ ገንዘብ (ሥጋን በተዋሐደ ጊዜ ) ግዙፍና ውሱን ነው።
#ዳግመኛም የእሳትና የብረት ተዋህዶ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
#የሕማሙ (የተቀበለው መከራ) አምሳል ነው።
#እንደ እሳቱ የማይዳሰሰው የማይያዘውና የማይጨበጠው #ረቂቁ መለኮት እንደብረቱ የሚዳሰሰውን የሚያዘውና የሚጨበጠውን ሥጋን በመዋሐዱ ነው ።
#እንግዲህ አምላክ ተያዘ ታሰረ ተገረፈ ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ ተነሳ አረገ #የምንለው በሥጋ ሞተ #በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ
( 1ኛ ጴጥ 3 ÷ 18 )
ስብሐት ለሥላሴ
ይቀጥላል
ቀሲስ ጥሩውኃ ክፍሌ።
78 viewszemari tiruwuha, 03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:27:59 እሁድ መርሐ ግብር አይኖርም።
83 viewsX, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:27:13 ነገ 3/11/2014 የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ በቅ/ኪዳነ ምሕረት ገዳም የሚካሔድ በመሆኑ ሁላችም በጊዜ መርሐ በግብሩ ላይ እንገኝ።
84 viewsX, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 11:07:43 ልዩ የምስራቅ ሐ/ሀ/ስ/የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የሚያዘጋጀው 14ኛው የሰንበት ተማሪዎች የጋራ ጉባኤ በሐረር መ/ጵ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ገዳም የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በሐረር ደ/አ/አ/ተ/ሃይማኖት ምዕራፈ ቅዱሳን ሰ/ት/ቤት አዘጋጅነት ይካሄዳል
በዕለቱም
###ቃለ ወንጌል
### ያሬዳዊ ዝማሬ
### ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ስልጠና
### መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ በዕለቱ ሊቀርቡ የተሰናዱ መንፈሳዊ መርሀ ግብራት ናቸው
የሰማን ላልሰማን በማሰማት በዕለቱ በአንድነት ስለ አንድነት ለመመካከር ቀጠሮአችን ከልዑል እግዚአብሔር ጋ በገዳሟ ይሁን
ልዑል እግዚአብሔር አንድነታችንን ይጠበቅ!!!!
136 viewsAntye Ante, 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 11:06:45
130 viewsAntye Ante, 08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 19:12:43 ክፍል (44)
#ነገረ ድኅነት
#ሰው በበደሉ ምክንያት ያ ተወስዶበት የነበረው ዘለዓለማዊው ሕይወት የዘለዓለም #ክብርና ነፃነት ተድላና #ሰላም #ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ በተዋህዶ ሰው ሆኖ #ወደዚህ ምድር በመምጣት #በፈቃዱ በተቀበለው
ጸዋትወ መከራና #ሕማም በፈጸመው #የድህነት ተግባር የተመለሰለት ቢሆንም
#ይህን ለመውረስ #ማመን #መታመን #መመስከር ይጠበቅብናል ።
#የክርስትና #መገለጫዎችም እነዚህ ናቸው።
#በክርስትና ሕይወት ሃይማኖትና ምግባር አይነጣጠልም #በሃይማኖት የእግዚአብሔርን #ህልውናና #የማዳን ሥራ አምነን እንቀበላለን ።
#በምግባር ደግሞ ለአመነው እግዚአብሔር እንታመናለን።
( ያዕ 2 ÷ 14 )
ሰው #ለአምላኩ የሚያቀርበው ግብሩ የሚገዛበት ዓይነቱና መታወቂያው ፍትወቱንና (ፍላጎት )
#ጉልበቱን በሚሰጥበት ምግባር (ሥራ ) ነው እንጂ #የጉልበት ድካም የሌለበትን ያቺን የልብ ሃይማኖት ብቻ ይዞ (ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ #በመጮህ የሚዞሩትንና ዕምነት በልብ ነው
እያሉ ከጾም ጸሎት የተራቋቱትን ማለታችን ነው) ።
#ምግባር የማይሠራ ሰው #በፈጠረው በአምላኩ የሚቀልድ
#ሥጋውን የሚወድ ብልጥ አምናለሁ ግን #አልገብርም የሚል ዐመፀኛ መሆኑን ማወቅ የገባዋል።
#የአፍ ሀብታም #የምግባር ድኃ ከመሆን አምላክ በቸርነቱ ይጠብቀን።
ስብሐት ለሥላሴ
ይቀጥላል
ቀሲስ ጥሩውኃ ክፍሌ።
148 viewszemari tiruwuha, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 16:27:27


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት እና በዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ!

'' ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ዕርገቱ ለክርስቶስ
እምድሓረ ተንሥአ እሙታን በአርብዓ ዕለት ወይባቤ በወቃለ ቀርን አማን መንክር ስብሐተ ዕርገቱ''

ሣምንታዊ ጉባኤ

በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀ መርሐ ግብር

የፊታችን እሑድ ሰኔ ፭
ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ
ዝማሬ
ትምህርተ ወንጌል
ስነ ጽሑፍ
ምክረ ካህንና ሌሎችም ስራዎች ተዘጋጅተው ይጠብቆታል።
ፈለገ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት
252 viewsX, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 10:00:25
ለመላው የሰ/ት/ቤታችን አባላት እንኳን ለአቡነ ሐብተ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዛሬዉ እለት በዓሉን በማስመልከት የዝክር መርሐ ግብር የተዘጋጀ በመሆኑ ሁላችንም ተገኝተን ከበረከቱ እንድንሳተፍ እናሳስባለን።

ዝክር ስላለ የአርብ ፀሎት እንዳይመሽብን ቀደም ብላችሁ 11:00 - 11:30 ድረስ ተገኙ።

የአርብ ፀሎት የሁሉም ሰ/ተማሪ እንደመሆኑ ሁላችንም የመገኘት ሐላፊነት አለብን።


ቅዳሜ ጠዋት ሶስቱም ክፍላት (ካዕላይም) ት/ት ይኖራቸዋል። ሁሉም ተማሪ 12:15 በመማሪያ ክፍሉ ዉስጥ መገኘት ይጠበቅበታል። መቅረት አይቻልም። በት/ት ምክንያት ከአገልግሎት ብትታገዱ ኃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

235 viewsX, edited  07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ