Get Mystery Box with random crypto!

በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቆመ በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየ | FastMereja.com

በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቆመ

በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየፈጸመ በመሸሽ ላይ የሚገኘው የሕወሓት ህገወጥ ቡድን በአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተጠቆመ።
የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው የአክሱም ከተማ የተገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ በ526 ሚሊዮን 860 ሺህ 200 ብር ወጪ የተገነባ መሆኑን፣ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለአገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሰፊ እንደነበር ተገልጿል።
የአየር ማረፊያው መጎዳት የአክሱም ሐውልትን ከጉዳት ለመታደግ የሚደረገውን የጥገና ስራ እንደሚያስተጓጉልና በርካታ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።
አውሮፕላን ማረፊያው በቱሪስቶች የሚታወቅ፣ በቀንና በምሽት አገልግሎት የሚሰጥ፣ የተሟላ እንደነበር ይታወቃል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነው።
------------
@fastmereja