Get Mystery Box with random crypto!

የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ሠራዊታችን በሁሉም ግንባሮች ድልን እየተጎና | FastMereja.com

የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ሠራዊታችን በሁሉም ግንባሮች ድልን እየተጎናፀፈ እንደሚገኝ አረጋገጡ ።

ጁንታው እያንዳንዳቸው 2 ሺ 500 የሰው ሀይል የያዙ 11 ብርጌድ ልዩ ሀይል ፣ 14 ብርጌድ የዞን ታጣቂ እና አንድ ብርጌድ ሚሊሻ ቢገነባም ፣ አሁን ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል ብለዋል ።

ጀግናው ሠራዊታችን በምዕራብ ትግራይ ከዳንሻ - ባዕከር ፣ አዲጎሹ ፣ አዲ ሀገራይ ፣ አዲጉዞምን ሰብሮ ትናንት ሽሬን መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል ።

በደቡቡ ግንባርም ከዋጃ ጀምሮ አላማጣ ፣ ኮረምን ይዞ ወደፊት ቀጥሏል ።

በምስራቁ ግንባር ፣ ጨርጨር ፣ መሆኔ ፣ ራያ ቆቦና ሌሎች ቦታዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል ። ጁንታውን ለህግ ለማቅረብም ግስጋሴውን ቀጥሏል ።

ነጻ በወጣው አካባቢ የሚገኘው ህብረተሰብ ለሠራዊታችን ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጀነራል ብርሀኑ አስታውሰው ፣ ህዝቡ ሠራዊታችንን ከሁዋላው እንዲመታ ቢያስታጥቁትም ፣ ምንም ሳይተኩሱ 200 መትረየስና ክላሽ አዲኮኮብ እና ሽሬ ላይ ለሠራዊታችን እስረክቧል ብለዋል ።

ጁንታው ኮማንድ ፖስቱን እና ትኳሾቹን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያደርግም ሠራዊታችን ነጥሎ ለመምታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል ።

በአሁኑ ሰዓት ጁንታው ኢትዮጵያን ወደ ጦርነት ለማስገባትና ለመበታተን ያቀደው እንደከሸፈበትና በመከበቡ ነፍስ አውጭኝ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል ሲል AMN ነው የዘገበው።
-------------
@fastmereja