Get Mystery Box with random crypto!

የቦምብ ፍንዳታዎች በባሕር ዳር ከተማ #FastMereja በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በተ | FastMereja.com

የቦምብ ፍንዳታዎች በባሕር ዳር ከተማ
#FastMereja
በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕር ዳር በተለያዩ አካባቢዎች የቦምብ ፍንዳታ መድረሱ ተሰማ ። የቦምብ ፍንዳታዎቹ ትናንት በተለይ ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 እና ቀበሌ 13 ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አካባቢ መድረሱ ተነግሯል ። በፍንዳታው በተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩም ተጠቁሟል ። በፍንዳታዎቹ ተማሪዎች መደናገጣቸው እና ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ቤት ለመውሰድ ሲሯሯጡ መታየታቸውን ዶቼ ቬለ ዘግበዋል።

ከፍንዳታው በኋላ ዛሬ በአንዳንድ ትምሕርት ቤቶች ፈተና ቢኖርም አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አለመሄዳቸውንም ዶቼ ቬለ አክሎ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በተለይ ቀበሌ 14 አካባቢ በምሽት መጠጥ ቤቶች አካባቢ በተከታታይ ቀናት ፍንዳታዎች ነበሩ ተብሏል ። ሌሊቱን ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ ማር ዘነብ በተባለው ቀበሌ የተቀበረ ቦምብ ፈንድቶ ከፍተኛ ንዝረት መከሰቱን የዶቼ ቬለ ዘገባ ያሳያል።

@FastMereja