Get Mystery Box with random crypto!

አርቲስት ዳንኤል ተገኝ የዲጅታል እቁብ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ #FastMereja ዲጅታል እ | FastMereja.com

አርቲስት ዳንኤል ተገኝ የዲጅታል እቁብ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ
#FastMereja
ዲጅታል እቁብ አርቲስት ዳንኤል ተገኝን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር በማድረግ የፊርማ ስነ ስርዓት ዛሬ ህዳር 17/2016 ዓም አድርጓል። የብራንድ አምባሳደር አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ለሁለት አመት በሚቆየው ውል ዲጂታል እቁብን በቢልቦርድ፣ በሚዲያዎች ላይ እንደሚያስተዋውቅ የተገለፀ ሲሆን ድጅታል እቁብን በመወከል የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት ድርጅቱን እንደሚያስተዋውቅ ተገልፇል።

ዲጅታል እቁብ እቁብን በዲጅታል መንገድ በማምጣት የነጋዴዎች እቁብ፣ የአሽከርካሪዎች እቁብ፣ የሰራተኞች እቁብ፣ የድርጅት እቁብ፣ የማህበረሰብ እቁብ፣ የአይነት እቁብ በተባሉ የእቁብ አይነቶች እየሰራ ያለ ተቋም ነው።

በአሁኑ ወቅት በቀን፣ በሳምንት እና በወር እቁብ የሚጥሉ ከ10ሺ በላይ እቁብተኞች እንደሚገኙ ተነግሯል።

@fastmereja