Get Mystery Box with random crypto!

ህፃን ልጅ የሰረቀችው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣች!! #FastMereja በማዕከላዊ ጎንደር ዞ | FastMereja.com

ህፃን ልጅ የሰረቀችው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣች!!
#FastMereja
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ህፃን ልጅ ወስዳ የጠፋችው በቁጥጥር ስር ውላ መቀጣቷ ነው የተነገረው የፍ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወ/ሮ አመልማል ተስፋሁን ለወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት እንዳስታወቁት ተከሳሽ ወ/ሮ ፈለቁ ጣሰው የተባለችው ግለሰብ ህፃን ልጅን ወስዳ ገንዘብ በመጠየቅ የማይገባትን ጥቅም ለማግኜት በማሰብ ሚያዚያ 22/2015 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 9፡00 በሚሆንበት ጊዜ በሻሁራ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ቀጠና 05 እየተባለ በሚጠረው ቦታ የቤት አከራይዋን የአቶ ግዛቸው አመራ ልጅ የሆነችውን ህፃን ረድኤት ግዛቸው የተባለችውን ህፃን ከረሜላ ልግዛልሽ በማለት በማታለል ሰርቃ ከተሰወረች በኋላ በተደረገው የፀጥታ አካላት ክትትል በአዲስ አበባ ፖሊስ ልዩ ቦታው እንጦጦ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በፍተሻ ጣቢያ ላይ ሚያዝያ 23/2015 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 2፡00 ሲሆን ህፃኗን ይዛ እጅ ከፍንጅ የተያዘች በመሆኑ በፈፀመችው የጠለፋ ወንጀል መከሰሷን ገልፀው የአለፋ ወረዳ ፍ/ቤት ግንቦት 24/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀለኛዋን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት በ7 ዓመት ከ2 ወር ፅኑ እስራት መቀጣቷን አስታውቀዋል፡፡

@fastmereja