Get Mystery Box with random crypto!

«ቃል የተገባላቸው ቤት አሁንም አለ ለማንም አልተሰጠም፣ አልተከለከሉም» የአዲስ አበባ መስተዳደር | FastMereja.com

«ቃል የተገባላቸው ቤት አሁንም አለ ለማንም አልተሰጠም፣ አልተከለከሉም» የአዲስ አበባ መስተዳደር
#FastMereja
ባሳለፍነው ሳምንት በሞት ያጣናቸው ታንክ ማራኪው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የተሰጣቸው ቤት ተከለከሉ የሚሉ መረጃዎች በስፋት ተደምጧል። ጉዳዩን አስመልክቶ ፋስት መረጃ ወደ ከተማ መስተዳደሩ ጥያቄውን አቅርበን ነበር።

ለሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ቃል የገባቹለትን ቤት ለምን ሳትሰጡት ስንል የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደርን ፋስት መረጃዎች ጠይቀናል!!

«በወቅቱ ለሻለቃ ባሻ የተሰጣቸው ቤት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ የሚገኘው ተገጣጣሚ ቤት ነበር እሳቸው ደግሞ ይህን አልፈልግም ግቢ ቤት ነው የምፈልገው በማለታቸው ነው ያልገቡበት ግቢ ቤት ያለው ቤቶች ኮርፖሬሽን እንጂ ከተማ መስተዳደሩ የለውም የተሰጣቸው ቤት አሁንም ለሌላ ሰው አልተሰጠም አለ» ብለውናል።

@fastmereja