Get Mystery Box with random crypto!

በጉጂ ዞን እንጨት ተሸክሞ ሲሸጥ የነበረው የ7 አመት ልጅ ምስሉ በፌስቡክ ከተሰራጨ በኋላ አሜሪካ | FastMereja.com

በጉጂ ዞን እንጨት ተሸክሞ ሲሸጥ የነበረው የ7 አመት ልጅ ምስሉ በፌስቡክ ከተሰራጨ በኋላ አሜሪካ የመማር እድል አገኘ
#FastMereja
ነገሩ እንዲህ ነው ገለታ ደምቦባ ይባላል 7 አመቱ ነው ጉጂ ዞን አዶላ ሬዴ የተባለ ወረዳ ጬምቤ የተባለ አከባቢ እንጨት ሲሸጥ ፎቶ ወጣ፣ ታሪኩን የተመለከተው አሜሪካ የአሪዞና ነዋሪው አበራ ቦጋለ የትንሹን ልጅ ታሪክ ለመቀየር መወሰኑን ለቢቢሲ ተናግሯል።

መጀመሪያ ላይ ልጁ እንጨት መሸጡን አቁሞ ወደ ትምህርት ቤት በመመለስ ከአንደኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ያለው ወጪ ለመሸፈን ነበር የወሰንኩት ይላሉ አቶ አበራ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከተወያዩ በኋላ ህፃኑን እዚያ ማስተማር የብላቴናው ቤተሰብ ችግር ውስጥ ስላለ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል ተስማማን ብለዋል።

«ከቤተሰቦቼና ከቤተሰቡ ጋር ተነጋግረን ልጁን ወደ አሜሪካ ወስደን ለማሳደግ ተስማማን» ብለዋል።

ልጁ እንጨት በመልቀም አንድ ሰዓት በእግር ተጉዞ ከተማ እንጨት ይሸጥ ነበር።

የሕፃኑ አባት አቶ ዳምቦቢ ዎዲቦ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አቶ አበራ ለልጁ ያሳየው መልካምነት እሱን ብቻ ሳይሆን የመንደሩን ነዋሪዎችንም አስደስቷል ብሏል።

@fastmereja