Get Mystery Box with random crypto!

የኦዳ ተማሪዎች በቻይንኛ ቋንቋ ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት ወጡ!! #FastMereja ባለፈው | FastMereja.com

የኦዳ ተማሪዎች በቻይንኛ ቋንቋ ውድድር ከአንድ እስከ ሶስት ወጡ!!
#FastMereja
ባለፈው ቅዳሜ የቻይና ኤምባሲ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በተካሄደው የቻይና ቋንቋ የንባብና የጥበባ ውድድር የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦዳ ልዩ አዳሪ ት/ቤት) ተማሪዎች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አሸንፈዋል።

“ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ቻይንኛ ተምሬያለሁ። በውድድሩ መጀመሪያ ላይ ፈርቼ ነበር። በኋላ ተረጋግቼ ችሎታዬን አሳይቼ አሸንፌ አንደኛ ወጥቻለሁ። በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች ውድድሩን በአንደኝነት ያጠናቀቀችው ተማሪ ሲያኔ ታደሰ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ለአሸናፊዋ ትምህርት ሲዘጋ ክረምት ቻይናን እንድትጎበኝ ጎብዣ አድርገውላታል።

የኦሮሚያ ልማት ማህበር በአዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ከመደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን የውጭ ቋንቋዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል።

በአገር ውስጥ አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ ይማራሉ፣ በተጨማሪም የአለምን ዋና ዋና ቋንቋዎች እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ቻይንኛ እና ፈረንሳይኛ ይማራሉ። እነዚህ ቋንቋዎች ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ ወደ ሥርዓተ ትምህርት ተካቶ ትምህርቱ እየሰጣቸው ነው።

@fastmereja