Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበበ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኢማሞች ህብረት የተሰ | FastMereja.com

የአዲስ አበበ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኢማሞች ህብረት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ አንዋር እና ኑር መስጅዶች ህዝበ-ሙስሊሙ ድምፅ በማሰማቱ ምክንያት በተከሰተዉ ችግር በሰዉ ሕይወት እና አካል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ብዙ ዜጎች በህግ ጥላ ስር ይገኛሉ፡፡
በሸገር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የመስጆዶች ፈረሳ ፍፁም ተገቢ ባለመሆኑ የምናወግዝ መሆኑን እየገለፅን የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የኢማሞች ሀብረት ጥያቄውን ያቀርባል፣
በተጨማሪም የኢማሞች ሀብረት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ እና ከዚህ ጋር በተያያዘ በምዕመናን ላይ የተወሰደዉን ተገቢ ያልሆነ እርምጃ በፅኑ እያወገዘ የሚከተሉትን ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥቷል፡፡
1. ከዛሬ ቀን ጀምሮ እስከ ዙልቂዕዳ ወር መጨረሻ ድረስ በሁሉም መስጅዶች ቁኑት እና ዱዓ አንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፣
2. በሁሉም መስጂዶች የፊታችን ጁሙዓ የኩጥባ ይዘት በሠላም፣ በአንድነት እና በሰብር ላይ እንዲያተኩር እና ህብረተሰባችን ይበልጥ በሚረዳው በአማርኛ ቋንቋ ዳዕዋ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
3. በነገዉ እለት ሐሙስ ዙልቂዕዳ 19 ፤ 1444 ዓ.ሂ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመፆም፤ በሰደቃ፣ በዱዓ እና በኢስቲግፋር ወደ አላህ በመቃረብ እና አላህ የተፈጠረውን ችግር እንዲያነሳልን እንዲለምን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
4. በተፈጠረዉ ችግር ሕይወታቸዉ ያለፈ እና የተጎዱ ቤተሰቦችን ሙስሊሙ ማህበረስብ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባዘጋጀው የባንክ ቁጥሮች እንዲረዳ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፡፡
5. በመጨረሻም የጁምዓ ሰላታችን በሠላም ተሰግዶ አንዲጠናቀቅ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ጥሪያችንን እያቀረብን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የመጣውን በላእ እንዲያነሳልን እና እንዲመልስልን እንለምነዋለን፣

አላሁ አክበር !!!
@fastmereja