Get Mystery Box with random crypto!

የትዳር አጋሩን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ፖሊስ በ 20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ! ተከሳሸ ረዳት | FastMereja.com

የትዳር አጋሩን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ፖሊስ በ 20 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ!

ተከሳሸ ረዳት ሳጅን መኳንንት ብርሃኑ በምዕራብ ጎንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የፖሊስ አባል ሲሆን ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓም በግምት ከምሽቱ 2:00 ሲሆን ነጋዴ ባህር ከተማ ከሚኖርበት ቤት የትዳር አጋሩ የሆነችውን ረ/ሳጅን ልክነሽ የትነበርክን በትዳራቸው በነበረ አለመግባባት ምክንያት በያዘው የጦር መሳሪያ በሰደፍ አንገቷን መትቶ እንድትወድቅ በማድረግ ጀርባውን በተደጋጋሚ በጥይት ተኩሶ በመምታት እንድትሞት አድርጓል።

የአዳኝ አገር ጫቆ ፖሊስም ምርመራውን አጣርቶ ለዞን ዐቃቤ ህግ የላከ ሲሆን ዐቃቤ ህግም የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539( 1-ሀ) በመጥቀስ በምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ክሰ በማቅረብ ሲከራከር ቆይቷል።

ተከሳሽም ወንጀሉን አልፈፀምኩም ብሎ የተከራከረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ህግን ማስረጃ ከሰማ በሗላ ዐቃቤ ህግ እንደክሱ ስላስረዳ ተከሳሹ የዐቃቤ ህግን ክስ እንዲከላከል እድል ቢሰጠውም የመከላከያ ምስክር የለኝም ስላለ ጥፋተኛ ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የዐቃቤ ህግን እና የተከሳሹን የቅጣት አስተያየት ካዳመጠ በሗላ ዛሬ በቀን 30/ 09/2015 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሹንና ሌሎችን መሰል የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ያስተምራል ያርማል ያለውን የ20ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ወስኖበታል።

መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ ነው።

@fastmereja