Get Mystery Box with random crypto!

«የጸጥታ ሃይሎች እያሰሩን ገንዘብ እየወሰዱና እያሰቃዩን ነው» የሸገር ከተማ ነዋሪዎች #FastMe | FastMereja.com

«የጸጥታ ሃይሎች እያሰሩን ገንዘብ እየወሰዱና እያሰቃዩን ነው» የሸገር ከተማ ነዋሪዎች
#FastMereja
የቀድሞ ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የነበረው አሁን የሸገር ከተማ አስተዳደር ተብሎ በዘንድሮ አመት ምስረታ ያደረገ ከተማ ነው። ከተማዋ ከተመሰረተችበት አላማዎች አንዱ ህብረተሰቡን በልማት ተጠቃሚ ማድረግ አንዱ ነው። ከተማዋ በስሩ የተለያዩ ክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች ተዋቅራ ተመስርታለች።

ነገር ግን ዘረፋ፣ ማስፈራራት እና በዘፈቀደ ማሰር የተለመደ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል የህብረተሰቡ ቅሬታ በፋስት መረጃ በዚህ መልኩ ይቀርባል።
እነዚህ ድርጊቶች በዋናነት የሚፈጸሙት በጸጥታ ሃይሎች ማለትም በፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ​​የወንጀል መርማሪዎችና የጸጥታ ሃይሎች መሆኑን ነዋሪዎች ለቢቢሲ መናገራቸውን ፋስት መረጃ ተመልክቷል።

በቡራዩ ከተማ ከ15 ዓመታት በላይ የኖረው ነጋሳ ለቢቢሲ እንደተናገረው በጸጥታ ሃይሎች ሁለት ጊዜ ተይዞ እንዲፈታ ገንዘብ መክፈሉን ይናገራል። የመጀመሪያ ቀን መጠነኛ የመኪና አደጋ ደርሶብኝ ወደ ሆስፒታል እየሄድኩ በሚሊሻ ተያዝኩ ከዛ ፖሊሶች በፓትሮል ይዘውኝ ሄዱ ምንም ሳልጠየቅ ታስሬ ቆየሁ ከዛ 20ሺ ብር ከፍዬ ወጣሁ ከወጣሁ በኋላ 10ሺ ብር ከፈልኩ በአጠቃላይ 30ሺ ብር መክፈሉን ነጋሳ ለቢቢሲ ገልፇል። የታሰርኩበትን ምክንያት ስጠይቃቸው ከተማ ቁጭ ብለህ ለሸኔ ሎጂስቲክ ታመቻቻለህ የሚል ምላሽ ሰጡኝ ነው የሚለው።

ሌላኛው አቶ ገምታ የተባለ አስተያየት ሰጪ ለቢቢሲ ሲናገር “የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ዜጎችን ማሰር እና ገንዘብ መቀበል የተለመደ ተግባር አድርገውታል። ወንጀል የፈፀመ አካል ከተያዘ እና ከተጠየቀ እኛም አንቃወምም። ነገር ግን ከዚያ ውጪ ይህ እየሆነ ነው” ይላል ጋምታ

ገምታ መንግስት ሰራተኛ ሲሆን ከስራ ወጥቼ ወደ ቤት እየሄድኩ እያለ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ታፍኜ ታሰርኩ ይላል በእስር ቤት ቆይታውም “ወንጀለኛ መርማሪዎች እና ፖሊሶች ሰዎች ከእስር ቤት ለመውጣት ገንዘብ እንደከፈሉ የሚነግሩበት ኮድ [ምልክት] አላቸው” ብሏል። ብዙ ሰዎች ለመልቀቅ ገንዘብ ከፍለዋል ይላል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ነቢራ ይባላል በሸገር ከተማ የግል ስራ አለው ከታሰረ በኋላ 100,000 ብር እንዲከፍል ቢነገረውም ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለአራት ወራት ያህል ታስሯል።

"መንግስት ለፖሊስ የሚከፍለው ህዝብ ለመጠበቅ ነው እንጂ ህዝብን ለመዝረፍ አይደለም" የፀጥታ ሃይሎች ዘረፋው የእለት ቋሚ ስራቸው እየሆነ ነው ብሏል።

ምርመራ ክፍል አስገብተው ገንዘብ ነው የሚጠይቁት እምቢ ካልክ ሸኔ ነህ፣ መሳሪያ ትነግዳለህ እያሉ የማታውቀውን ነገር ይለጥፉበሃል ብሏል ረቢራ።

ሁሉም ታሳሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፍርድ ቤት ቀርበው እንደማያውቁ ግማሹ ከፍሎ እንደወጣ አልከፍልም ያለው ለወራት ታስሮ እንደተለቀቁ ነው የሚናገሩት።

ቢቢሲ የሸገር ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ሃላፊ ኮማንደር ሌንጂሶ ጆቴ ከነዋሪው በጸጥታ ሃይሎች ላይ ስለቀረበው ክስ ጠይቋል ተጠይቀው ይህን ብሏል "የሸገር ከተማ 12 ክፍለ ከተማ እና 36 ወረዳዎች ያሏት ሲሆን እስካሁን ድረስ እንዲህ አይነት ቅሬታ አላገኘንም" ብሏል።

"ማንም ሰው በአካል መጥቶ እኔንም ሆነ ለሌሎች ጥቆማ ሊሰጠን ይችላል" ብሏል።

አሻዋ ሜዳ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ በጸጥታ ሃይሎች ህዝቡን እያስፈራሩ እና እያሰሩ በማሰቃየት "ቤርሙዳ" የሚል ስያሜ ወጥቶለት ነበር አሁን የሸገር ከተማ ከተመሰረተች በኋላ በፖሊስ ጣቢያ የስነምግባር ችግር ባለባቸው የጸጥታ አካላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ኮማንደር ሌንጂሶ ተናግረዋል።

ዘገባው ረጅም ሲሆን ቀሪው በቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ላይ ይገኛል።

@fastmereja