Get Mystery Box with random crypto!

*** በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በንብረት ላይ የሚጣለውን ግብር ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ | Farankaa - ፈራንካ

***
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በንብረት ላይ የሚጣለውን ግብር ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ የፌደሬሽን ምክር ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጽድቀውታል።

በንብረት ላይ የሚጣለውን ግብር ባለቤትነት ለመወሰን የፀደቀው ሀሳብ በሀገሪቱ ዘመናዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ለመገንባትና ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዲኖር ለማድረግ ትልቅ መሰረት የሚጥል ነው ተብሏል።
እንደ ሀገር አራት መሰረታዊ ችግሮችን የሚፈታ ነው የተባለለት ውሳኔ በንብረት ላይ የሚጣለው ግብር ኢ-ፍትሀዊነትንና ሌብነትን ለመከላከል አቅም የሚፈጥር እንደሆነም ተጠቅሷል።
ውሳኔው በተጨማሪም የታክስ ስርዓቱን ለማስፋትና የከተሞችን አቅም ለማጠናከር ዕድል ያለው መሆኑም ተመልክቷል።

በፌደራል ፍ/ሕ ምርምር እና ሥልጠና ኢኒስቲቲዩት የንብረት ታክስ ምንነት እና ባሕርያት በሚል ርዕስ ከሶስት ዓመት በፊት ያጋራውን ጽሁፍ ለአጠቃላይ ግንዛቤ ከዚህ እንደሚከተለው አጋርተናችኋል ።
ፅሁፉ ረጅም ቢሆንም ጥሩ ግንዛቤ የሚሰጥ በመሆኑ በትዕግስት አንብቡት ።