Get Mystery Box with random crypto!

ለሊዝ ፋይናንሲንግ ብድር ስታመለክቱ ቢዝነስ ፕላን ወይም የአዋጪነት ጥናት ብቻ አቅርባችሁ ሳይሆን | Farankaa - ፈራንካ

ለሊዝ ፋይናንሲንግ ብድር ስታመለክቱ ቢዝነስ ፕላን ወይም የአዋጪነት ጥናት ብቻ አቅርባችሁ ሳይሆን ሙሉ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ጭምር አያይዛችሁ መሆን ስላለበት ለማመልከት ስትመጡ ቀጥሎ በተቀመጠው ዝርዝር መሠረት አሟልታችሁ መሆን እንዳለበት እናሳውቃለን፡፡

የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ዝርዝር (በስራ ላይ ያለው)

ክፍል አንድ፡- አስገዳጅ መስፈርቶች (Mandatory Requirements)
1.1 ማመልከቻ፡-
1.1.1 የሊዝ ማመልከቻ

የባንኩ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የሚፈልጉ አመልካቾች ጥያቄያቸውን የሊዝ መጠኑንና ሊገለገሉበት ያቀዱትን የካፒታል ዕቃዓይነት በመጥቀስ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
1.1.2 በባንኩ የተዘጋጀውን የሊዝ ማመልከቻ ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

1.2 ፈቃድ ( በስራ ላይ ያለ ድርጅት ከሆነ)
1.2.1 የንግድ ሥራ ፈቃድ
1.2.2 የዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት
1.2.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር

1.3 መሬት /የማምረቻ ቦታ/
1.4 ዋጋ ማሳወቂያ ሰነድ /Pro-forma Invoice/

ለሊዝ አገልግሎት ለሚቀርብ ጥያቄ ከሶስት አስመጪ ወይንም አቅራቢ ድርጅቶች የተሟላ የዋጋ ማሳወቂያ ሰነድ መቅረብ ያለበት ሲሆን ለሊዝ አገልግሎት ለሚቀርብ ጥያቄ የአዋጭነት ጥናት ለማከናወን አመልካቹ አንድ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ካቀረቡ በቂ ይሆናል፡፡

1.5 የተሳትፎ የምስክር ወረቀት፡- በባንኩ የተዘጋጀ ስልጠና የወሰደ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡

1.6 የንግድ ዕቅድ ወይም የአዋጭነት ጥናት ማቅረብ አለበት፡፡
1.7 የድርጅቱ /የግለሰቡ መዋጮ፡
1.7.1 ለስራ ማስኬጃ ወጪ መሸፈኛ የሚውል የ20% መዋጮ በጥሬ ገንዘብ የሊዝ ዕቃ ጥያቄ እንደተፈቀደ በባንኩ በሚከፈት ዝግ ሂሳብ ገቢ ለማድረግ ሰለመስማማታቸው በጽሁፍ ማረጋገጥ፡፡
1.7.2 የመዋጮ ገንዘብ አጠቃቀምን በተመለከተ ባንኩ በሚያስቀምጠው ዕቅድ መሠረት ስራ ላይ ለማዋል መስማማታቸው የጽሁፍ ማረጋገጫ፡፡
ክፍል ሁለት፡- እንደ አስፈላጊነቱ /እንደሁኔታው (Optional Requirements) ተያይዘው የሚቀርቡ ተጨማሪ ሰነዶች፡-
2.1 ውክልና (ስልጣን)
በሶስተኛ ወገን የሚቀርብ የሊዝ ፋይናንስ ጥያቄ /ማመልከቻ ከሆነ አግባብ ካለው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ባላቸው ወኪሎች መቅረብ ይኖርበታል፡፡
2.2 የቅድመ ሥራ ታሪክ መዝገብ (Track Record)
2.2.1 ሊዝ ጥያቄአቅራቢው
በስራ ላይ የሚገኝ
አዲስ ስራ ጀማሪ
አመልካች በስራ ላይ ከሆነ ፡-
 የግብር ግዴታ ማስረጃ
 የሂሳብ መግለጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2.2.2 የሂሳብ መግለጫ፡- ከሶስት ዓመት ያልበለጠ ጊዜያዊ /ያልተረጋገጠ የሂሳብ መግለጫ (Provisional Financial Statements) ወይም በተፈቀደላቸው የሂሳብ መርማሪዎች የታየ (የተጣራ) የሂሳብ መግለጫዎች (Audited Financial Stateme\ \nts) ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን አዲስ ሆኖ የንግድ ስራ ላይ ካልሆነ ግን የግብር ግዴታና የሂሳብ መግለጫ ማቅረብ አይመለከተውም፡፡
2.3 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ፡
አመልካች በግል ይዞታ ላይ የሚሰራ ከሆነ እንደ ኘሬጀክቱ ዓይነት እና ሁኔታ ከሚመለከተው አካል የማረጋገጫ ድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡
ነገር ግን የሚሰራው በመንግስት ማምረቻ ቦታ ላይ ከሆነ ተከራዩ ይህ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ማስረጃ ማቅረብ አይገደድም ሆኖም የማምረቻ ቦታውን የገነባው የክልሉ መንግስት ተገቢውን የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ስራን ያከናውናል፡፡