Get Mystery Box with random crypto!

ዕለተ ሐሙስ ላይ ነን። ተላልፈን የተሰጠንበት ቀን ላይ። ከእኛ ጋር ማዕድ የቆረሰ፣ ከእኛ ጋር በአ | የፋኖ የሚድያ ዘመቻ

ዕለተ ሐሙስ ላይ ነን። ተላልፈን የተሰጠንበት ቀን ላይ። ከእኛ ጋር ማዕድ የቆረሰ፣ ከእኛ ጋር በአንድ ምንጣፍ ተቀምጦ የተማረ፣ እኛ የሾምነው እኛ ያከበርነው ..... ለፈሪሳውያን የሸጠበት ቀን ላይ ነን።

ተሽጠናል። ገና ይተፋብናል።
ገና እንጀራችንን የበላ ሕዝብ ስቀለው እያለ ይጮሀል።
ገና 6666 ጊዜ እንገረፋለን።
ገና በጅራፍ ብዛት ሰውነታችን በደም ይጠመቃል።
ገና መስቀል ተሸክመን ወደ ቀራኒዮ እንጓዛለን።
መስቀል ተሸክመን ገና 13 ጊዜ እንወድቃለን።
የእሾህ አክሊል ደፍተን.... እጅ እግራችን ተቸንክሮ በዕለተ አርብ ገና እንሰቀላለን።
ገና ኮምጣጤ ይጠጡናል።
አዎ ነፍስና ስጋችን በመስቀሉ ላይ ይለያያሉ።
አዎ ቅዳሜን በከርሰ መቃብር እናሳልፋለን።

ግን በዕለተ እሁድ መግነዝ ፈቺ..... መቃብር ከፋች ሳንጠራ ..... በድል ትንሣኤያችን ይሆናል።

የመስቀሉ መከራ መጀመሪያ ላይ ነን። አሳዳጆቻችን በአሸናፊነት ስሜት የሚደነፉበት ሰዓት ላይ ነን።
ግን ገና መሰቀሉም፣ መቀበሩም፣ ትንሳኤውም ይቀራል።

ቤተ ክርስቲያኔን ሊያጠፋ የመጣን ጠላት መክቼ..... በቤተ ክርስቲያኔ ደጃፍ መስዕዋትነትን እቀበላለሁ።

መሞት ብቻ ሳይሆን መክቶ መሞት

እስከመጨረሻው ትንሳኤ ድረስ መከራን ሁሉ ስለ ሃይማኖታችን.... ተጋድሎን ሁሉ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንቀበላለን።


@MereidAmhara
@MereidAmhara