Get Mystery Box with random crypto!

በዋሺንግተን ዲሲ ስለተጠራው ሰልፍ..... የኔ ምልከታ የኦቶ ሳዊሮስ የኦሮሞ ሲኖዶስ ማቋቋም | የፋኖ የሚድያ ዘመቻ

በዋሺንግተን ዲሲ ስለተጠራው ሰልፍ..... የኔ ምልከታ

የኦቶ ሳዊሮስ የኦሮሞ ሲኖዶስ ማቋቋምን በተቃውሞ ሰልፍ ለመቃወም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እየተንቀሳቀሰ ያለው ግብረ ሃይል ቀናነቱን ባደንቅለትም አለማስተዋሉን ግን እነቅፈዋለሁ።

እስከ አሁን ስንት ሰልፍ ወጣን
ስንት አደባባይ ላይ ተሰጣን

ወለጋ ላይ ለሚያልቀው ሕዝብ ሰልፍ ወጣን። ለታገቱት ተማሪዎቻችን ሰልፍ ወጣን። ስለ አዲስ አበባ ሰልፍ ወጣን። ስለ መተከል ጭፍጨፋ ሰልፍ ወጣን። ስለ ማይካድራም ስለ አጣየም ተሰለፍን።
....... ግን ምን ለውጥ አመጣን
ተቋውሟችን ከምን ደረሰ
ምን ለወጠ ምን አሻሻለ

አሁን ደግሞ ስለ ቤተ ክርስቲያን ልንሰለፍ ነው። ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ በየሃገሩ፣ በየኤምባሲው ደጃፍ እንደተደረጉ ሰልፎች አሁንም ምንም የምንለውጠው፣ ምንም የምንፈጥረው፣ ምንም የምንቀዳጀው ድል የለም።

ሰልፍ እንወጣለን። መፈክር እናሰማለን። ባነር አሳትመን እንሰቅላለን። በአደባባይ ያሳየነውን ትርጉም አልባ ተቃውሞ You Tube ላይ ጭነን ታግለናል ብለን እንኮፈሳለን።

ጠላቶቻችን በሌሊት ተደራጅተው በቀን ያጠቃሉ።
በየገቡበት ቦታ ከብረት ሽቦ የጠነከረ ኔትወርክ ዘርግተው ሁሉን ይቆጣጠራሉ።

እኛ ግን ዛሬም መንግሥት እጅህን አንሳ እንላለን።
ለማስታወስ ያህል መንግሥት እጁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ ማንሳት ቢፈልግ የኛን ሰልፍ አይፈልግም ቀድሞ ያነሳ ነበር።

የሚያስፈልገው መደራጀት ነው። ከብረት ሽቦ የጠነከረ ኔትወርክ መዘርጋት ነው። የመንግሥትን ሰላዮች ነጥሎ መምታት ነው።

How many times ስንሰለፍ ልንኖር ነው ወገን። ኧ..ረ እ.የ.ነ.ቃ.ን.

ተቀላቀሉ


@MereidAmhara
@MereidAmhara