Get Mystery Box with random crypto!

ሕያው ከሰራነው ንጣፍ.. ርቀት ፀንቶ ላይቆም በራሱ እያመነ ክፍተት ባንቺ ገላ እየተሸፈነ | ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ሕያው

ከሰራነው ንጣፍ..


ርቀት ፀንቶ ላይቆም በራሱ እያመነ
ክፍተት ባንቺ ገላ እየተሸፈነ

ጥግት..

ፍርሀት እጅ ሰ'ቶ
የኔና አንቺ ክንዶች ነፃነት ቀንቷቸው አንዱ ባንደኛው ላይ
ስህበት ድል ነስቶ ከጥጋታችን ውስጥ ነፋስ መውጫ ላላይ

እቅፍ..

በእቅፋታችን ስልት በላብ ወዝ መጣበቅ መላቀቅን መናቅ
በዕምነት ልክ ማየት አንድ ሌሊት መኖር እልፍ ነገን ሳናቅ

ጥብቅ..

አንድ መሆን አይነት ያንቺን ትንፋሽ መማግ ውስጥሽን መተንፈስ
ያንቺን ህልም ማለም መኖር ያንቺን መንፈስ

ዋህድ..

ሌላ ገፅ ውህደት መዳፌ ካካልሽ ወደ ልብሽ ግድም
እንዲህ ባ'ለ ውበት የተኖረ ምሽት ቢነጋም አይገድም።

ጥፍትት..

@merekkk




╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza