Get Mystery Box with random crypto!

ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

የቴሌግራም ቻናል አርማ faiza_kiza — ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗
የቴሌግራም ቻናል አርማ faiza_kiza — ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗
የሰርጥ አድራሻ: @faiza_kiza
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.22K
የሰርጥ መግለጫ

ማወቅን ማወቅ ፣አለማወቅን ማወቅ ፣አለማወቅን አለማወቅ ፣ማወቅን አለማወቅ፣ አለማወቅን ማወቅ ነዉ፡፡ (sokrats ) @faiza_kiza
በብዕር እንነሳለን በብዕር እንዘቅጣለን በብዕር እናድጋለን 👍🥰
አስተያየቶቻችሁን በ @mornin_bot አድርሱኝ
Support me on https://jami.bio/faiza

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-12 22:53:54 ሁሉም ለምን ያልፋል?
( በእውቀቱ ስዩም)

የጣፈንታ መዳፍ
ደስታና መከራን: እያፈሰ ሲናኝ
"ሁሉም ያልፋል " ብሎ : ማነው የሚያፅናናኝ?
ግራ በተጋባ :በዞረበት አገር
ካንቺ የምጋራው :ሰናይ ሰናይ ነገር
ፊቴን የሚያበራው :ያይንሽ ላይ ወጋገን
ዛሬ ተለኩሶ : የሚያሳየኝ ነገን
ለምን ሲባል ይለፍ : ያንን መሳይ ፍቅር
ደሰታሽ ይገተር: ሳቅሽ ቆሞ ይቅር!!
በብሩህ ቀላማት የተሸላለመ
-የተዋበ ህልሜ
በሁለት ጦርነት: መካከል የቆመ
-አጭሩ ሰላሜ
ያፍላነት ወኔየ : የጉርምስና አቅሜ
ነበር ተብሎ እንዳይቀር :እንዳገኘው ወትሮ
ባለበት ላይ ይቁም :ባስማት ተገትሮ::
እና
ከጣፈንታ መዳፍ: ሞልቶ ከሚፈሰው
በሰው የሚደርሰው
ለሰው የሚደርሰው
በጊዜ ኬላ ላይ : ተዛዝሎ ሲሰለፍ
በጎ በጎው ይቆይ : ክፉ ክፉ ይለፍ!!

...

ሕያው

ወደ ምንም..


ህመም ፀናሽ ስሱ ልቤ ሀያል ሆነ ጣር አወቀ.
ያ'ይኔ ጀርባ የ'ምባ ኮዳ ከረጢቱን አደረቀ.
ደነደነ አካላቴ የደም ጭቃ ተላመደ.
የገላዬ እርጥብ ጠረን የግፍ እጣን ጪስ አወደ.
ወደፊቴ ተካካደ ከህልሜ ዓለም ከነገዬ.
ተስፋን ተፋሁ ከናካቴው እኔም ሞትኩኝ ከዘገዬ.

እኔነቴ..
በቃ እንግዲህ እንጃለቱ ሰውነትን ከሰበረው.
እንደ ምንም ተፈጥሬ ምንምን ነው የምኖረው..


...


" ጥበብ እውነትን ለማጉያ የምንጠቀምበት የውሸት ዓይነት ነው። "

#ፀሐይ ለምን ቢጫ ሆነች?


" ቢያንስ ራሳቸውን ሲያዳምጡ አይረባበሹም። "

#ባልንጀሮቹ

" እንደ አህያ ሥጋ አልጋውን ትቶ አመድ ላይ የተንከባለለው ሰውዬ፣ በአመዳሞቹ ግዛት ደግሞ ሌላ ትርጓሜ እንዳለው ማን በነገራቸው። ማን በነገራቸው አመድ የወርቅ እኩያ እንደሆነ በዛኛው ግዛት።"

#ፍፁም

" ምንም ነገር እኮ በመሠረቱ አይጠፋም። ጨክኖ ያለ-መፈለግ ወይም ያለመፈለግ ይሆናል እንጂ ...ምንም ነገር ፈላጊ ካለ እኮ ጨርሶ አይጠፋም።"

#የሩሲያ ፎቶግራፎች

" ምንም ነገር የማያረባ ሰው አይረባም ይላሉ። ወይ ልጅ፣ ወይ ብር፣ ወይ ስም፣ ወይ እውቀት፣ ወይ ጽድቅ ... ሰው እስከሆነ የሆነ ነገር ማርባት አለበት ባይ ናቸው፤ ባዮቹ። ካልሆነ "አይረባም!" "

#ግስ አርቢዎቹ

"ይመስላል ዘላለም" ከተሰኘው የደራሲ ሌሊሳ ግርማ መፅሀፍ በሀይላይተራችን ከተቀለሙት የተቀዳ።
280 viewsBell, 19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:07:35 ☞ ዝክረ ኸሚስ ( 85 )
.
« ጉረስ ያለውማ ማድ የዘረጋለት ፣
በእህል ውሃ ዲስቱ ኒካውን ጣደለት ። »
( አገሬው )
-
አውገረዴ ሆዴ ...
አብሮ ዘማች ጓዴ ፣
ኸሚስ አመሻሹ - - ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ያርገበግበኛል የክድሚያሽ ወጋገን ክንፉን እያማታ።
.
ይሄው ...
.
ወቅቱ ላይ ደግ ሀጃ ፣
ሃጃው ላይ ውብ ሓድራ ፣
ሓድራው ላይ ጠይም ሌት ፣
አንቺን የተኳለ በቀለሜ አውሃል የሚያክለፈልፈኝ፣
ለሰንበራም ግጥም ፣
የነፍሴን ዳርቻ በኣጀቡ ለበቅ በጉድ የሚገርፈኝ ።
..
( መቼስ ...
..
እድል ባያነቅፈኝ እጣዬ ጠርጎልኝ ፣
መንገዴ ቢያሰልጠኝ ‘ርምጃ ሰልቶለልኝ ፣
ብቻየን አይሆንም ...
ውሃ ልኬ አንቺ ነሽ ፣
የመሄዴ ሚዛን ከነግ ተስፋ ፈጅር ተዋዶ ይተጋል፣
በ‘ያንዳንዱ ዳና የመድረሴ ጀንበር በሺህ ዲጂት ያድጋል።
..
ኸሚስ አመሻሹ ...
ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ሃጃው ገድምዳሜ ፣
ሓድራው አባ ሞገድ ፣
የቀኑ ምስለኔ የለይሉ ባለሟል ጠይሞ አንቺን ሲሆን ፣
በኸሚሱ ሞደብ የቱን ቀለም ይዤ የቱን እጥል ይሆን ?!
.
( እንዲያ ሆነ እንግዲህ ... ! )
.
እድያ ነውና ...
እምቢ የማይሉት ፣
ሀቅ ያጉረበረበው ምናብ ሲጠዘጥዝ እከኩ ይነሳል፣
ጠይም ሌሊት መሀል ፣
ቀልብ የሚያለመልም ሀረግ ያፈረጠው ቅኔ ደም ይፈሳል
.
አዎ !
( አውቅሻለሁ ሌቱን ... ! )
.
በሀጃው ኸለዋ ፣
ከግርዶሹ ወዲያ አወል ቡናው ደርሶ ቀሃ ጀባ ‘ስኪባል፣
ከመከኬው ክንፈር ፣
ከፍንጭትሽ ግርጌ ፈገግታሽ ያደባል።
ሊናደፍ ...!
.
መገን ።!
.
ፈሽረክ ትይዋለሽ ...
.
መሳቅሽ አቅል ነው !
ፈገግታሽ ቀለብ ነው !
.
የመሀባ ሸውቁ ፣
የሓድራውን ዋርካ ፣
በፈገግታሽ ጠለሽ ሌቱ ላይ ያዘማል፣
ሳቅሽን አሳቦ ....
ነፍስ የሸነቆረው የሀሴት ጉድ ቀለም ፈሶብኝ ይተማል።
..
አውገረዴ ሆዴ ፣
ኸሚስ ሃላል ሳቄ ፣
ጠይም ሌት ቀለሜ ፣
ገራም ማልዶ ቢብት ፣
ለይሉ ቢገማሸር ታለ ሰው ብቻውን በዱንያ ሞደቡ፣
ቀለሙ ጥሞናን በሶብሩ ቢያረብብ ምን ቢቸር አደቡ፣
.
ቀኑ መች ሲቀናው ፣
ሌቱ መች ሲገራው ፣
ሊገጥመው ሰው ገጥሞት ፣
ከኸልቄው እዬዬ እምባ እየጨለፈ ፣
ዝጎ ላይዶለዱም ለብዕሩ ስለት ሳቅ ካላጠቀሰ ፣
ገጣሚ ፉዞ ነው ... !
ለምናቡ ንቃት ሰውነት ኮልኩሎት ካልተቀሰቀሰ ።
ገጣሚ ‘ራስ የለው ... !
ለምናብ ጎፈሬው ባብሮነቱ ሚዶ በሰው ካልነቀሰ፣
.
ኸሚስ አመሻሹ - - ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ያርገበግበኛል የክድሚያሽ ወጋገን ክንፉን እያማታ።
..
እንግዲህ ...
እሱ ይደግሰው ፣
አይሆንም ታለ ሰው ፣!
እንኳን ሳቁ ቀርቶ ይግጠመኝ አህህ ይብለገኝ እዬዬው፣
በግጥም ላባብል በምናቤ አንቀልባ ስለ ሰው አዝዬው።
.
« አዳኝ ቁንጥር ፈርቶ -- ጭቃ ተጠይፎ ፣
አይወረወርም -- ቀስቱ ደጋን አልፎ ። »
.
እያለኝ በቅኔው አያ ሙሌ ጓዴ ፣
እንደት ሀቅ ልዘጋ ይቻለኛል እንዴ ?!
.
እሱ ይዘንልኝ ፣
ሙሾ ተቧልት ጋር ፣
እንደህል ዋጀራ በማይለይበት ፣
ዘለላ ቃል ሳልፅፍ አዝሞ እንዳይነጋ ባክኜ ‘ ንዳይፈጅር ፣
መሷረፊያ ቀለም አንዳቹን ዛር ልኮ ለፍርጃው ይጀርጅር ።
..
ታልቸረማ ምኑን ...
ከምኑ ተጋጥሞ ፣
ሌሊቱ እንደት ጥሞ ፣
ሰው ታላስባለማ በምን ወዝ ሊከተብ ሀቅ እንዳይቀበር ፣
ቅብጅር ነው ‘ንጂ ፣
ሌት ሌላ መልክ የለው ካልጠየመ በቀር ።
---
semir ami


@semiraklu
520 viewsSemir ايمي, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 22:47:02 መ ረ ቅ:
ሄዶን

ሙዚቃ እየሰማን ያሳለፍነው ደስታ
ላንቺ ብቻ ሆነ መንፈሴ ትዝታ
እሩቅ ያለሺው ግማሽ ሰውነቴ
በቃ ተለያየን ተቆረጠ አንጀቴ
(ዘፈን)

- ግለ ወሲብ ታውቃለህ?

- አውቃለሁ!

- ምንድን ነው?

- ፈገግ ብሎ ... ግብረ መዳፍ ማለት መሰለኝ! አለ።

- ከገዛ ገላህ ጋር ተዳርተህ ታውቃለህ?

- በስመአብ!! ድንጉጥ ማማተብ ታየበት! ምን ማለት ነው እሱ ከገዛ ገላ መዳራት?

- እስቲ ግም አትሁን! ጥያቄ አይደል እንዴ የጠየቅኩህ? ዘፈን በሌለበት እስክስታ ይቀናሀል!!

- ከዚህ በላይ ዘፈን? ሀሳብህ አልገባኝም።

- ይሄ ሀሳብ አይደለም! ታሪክ ነው።

- ታሪክ?

- እንደ ነገሩማ
እድሚያችንን ቀድመን ነበር ም'ናረጂ
ያማልክቱ ፀሎት ቢጠብቀን እንጂ።

እንደ ነበሩማ
ሞተን ነበር ሞትን መሞትን ቀድመን
እድሜ አማልክት ሆኖ እድል ባይጀባን።

- እድል? ለምን ታወዛግበኛለህ?

- አትለጠፍ!!

- ቀጥል ልስማህ...

- እንትሰማኝ ባይሆንም አወራለሁ። ታሪክ ልንገርህ?

- የምሰማው ነው የምታወራው?

- ነገር ቶሎ ይገባሀልና?

- በላ እያወራህ!

- ባለ አራት ገፅ ሺ ታሪክ
ገፅ አልባ አንድ እውነት

- ከእውነታዎች ገዝፎ ቢታወስ ጊዜ...

- ደሞስ በሳል ነህና?

- በልማ አውጋኝ!!

.
.
.

ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ...
.
.
.
ሄዶን

#ገፅ አንድ
ርዕስ የለውም!(ርዕሱ አይደለም።)

አጀብ ቢያውረው ቅንዝር ምንዝሬን
ተፈተለኩ ወደ ምድጃሽ
ባይበርደው ገላ መሞቅ ወጉ ነው
ፈቀድኩሽ ስልሽ እሺ በይ ከቻልሽ።

= አማልክቱ ጣልቃ ገብተው "ላስብበት" ብትል ጊዜ እሳቱ ጠፋ።

#ገፅ ሁለት
ፈቃድ አልባ ፈቃድ

ረመጥ ሳሳድድ ዘልቄ ከርስ
ፍም መስላ ቆመች እፊት ለፊቴ
እፍ እፍ ልበል ይብሰል መፍቀዷ
አንድም ለነፍሷ አንድም ላንጀቴ።

= አማልክቱ ጣልቃ ገብተው ንቃቴን ቢሰልቡት እፍ እፍታው በቀናት ተገምዶ መፍቀዷን አሳረርኩት መሰል።

#ገፅ ሶስት
ሰላቢ እውነት

ባጉል እፍታ ሲያር የከረመ
ሙት ያየ ገላ እንባ ሳይንደው
ነገን ያመነ ኩታ ደርቦ
ና ሲሉት ሄደ ወደ ወደደው።

= አፈሩ መልኩን ሳይቀይር አማልክቱ ጣልቃ ገብተው ተስፈኛ ኩታ የሸፈነውን በቋፍ የቆመ የከሰል ሀውልት ይነቀንቁት ጀመር።


.
.
.

ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ ...
.
.
.
ሄዶን

#ገፅ አራት
ተራማጅ ግዑዛን

አጀብ ያነገተ
ክንድ አልባ ጨርቅ አርጓል
የጉልበት ቁልቁለት
ወ'ዳይኖች ያርጋል
ወዲያ ካ'ስፋልቱ ዳር
ትዕንግርት ይፈልቃል
የፈረሰ ገላን በጉያው ሸክፎ
በነግ የተተካ ነጠላ ይስቃል። ...

= አማልክቱ ፈንጠር ፈንጠር ብለው ያስካካሉ።

ምንስ ይሆን ሸረቡ?
የትስ ይሆን መረቡ?
ማንስ ያያል ቢያውቀው?
ማንስ ያውቃል ቢያየው?
ምነው? ምነው?

#ከፍርሀት ባሻገር

ፀንሻለሁ ብል ተኝቶኝ ስጋት
ነግ በኔ ብለው ደጄን ላይረግጡ
ኳ! ባለ ቁጥር ሽብር ሸመታ
ምን በጀ ማርገዝ ምን በጀ ምጡ?

ብዬ
ራሴን በጀርባዬ አዝዬ
እጄን ከ'ጇ ጣል ባረገው
...

= እሳት የራበው የከሰለ ገላዋ ቀዝቅዟል። የቀዘቀዘን በስሱ ትጎነጫለች: አከላቷን ሸብሽባ ጥግን ተጠግታለች። ራሷን አሸማቀቀች ወይስ ራሷን ከለከለች? ጥያቄዎች እንደ አሸን መፍላት ጀምረዋል። ከነበር የተማረ ልብና ዛሬን ያመነ አዕምሮ ግን ከጥያቄዎች ባሻገር፤ ካ'ድካሚው ጉዞ ማበቻ ፤ ከምልጃና ካሳ ዕርገት ፤ ፍቅር ውስጡ የደበቀ ስርቻ ይታያቸው ነበር። ጥንድ አቅም ስርቻ።


ዝምዝምታ አየሩን ሞላው
መልስ አዝኗል ብቻውን ቀርቶ
ቢመኝስ ማን ይድረዋል?
ጥያቄን ጥያቄ አግብቶ።

= አመፀኛ ወኔ ከዝምታ ተጋፍቶ መፍቀዷን ጠየቀ። ሀፍረት የለበሰ ገጿን ወደ መሬት ደፍታ ...
አንዳንዴ... ለመፍቀድ ከፍቅር ይልቅ ስብዕና ይቀድምና የሴትነት መለኪያ መስሎ ያታልለናል። ከመውደድ ስም ይቀርብና ካመኑት ሳይሆን ካወሩት መዋል፤ ካወሩት መታየት ፍቅር ይሆናል።(ይመስላል።)

እንዲያ ነው የሆነው
እንዲያ ነው የሆንኩት
አርጓል ፍቅርህ ካልነበረበት
ኦና ነው ልቤ ውስጡ ቢከፈት።

.
.
.
ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ ...
.
.
.
ሄዶን

ባዕዱ እውነታ ከመሻቴ ባያስጥለኝ፤ መፍቀዷን ዳግመኛ ተማፀንኩት።


ጨው ቀመስ ቃልሽ ለጆሮዬ የመረረኝ
ባዕድ ምላሽሽ ከመሻቴ ባያስጥለኝ
ፈቃድሽን ልማፀነው ብንበረከክ
ረዳኝ እንጂ ልሞ አፈሩ
ስር ጉልበቴን መች ሻከረኝ?

ትጠየቅ!

ፀንሻለሁ ብል ተኝቶኝ ስጋት
ነግ በኔ ብለው ደጄን ላይረግጡ
ኳ! ባለ ቁጥር ሽብር ሸመታ
ምን በጀ ማርገዝ ምን በጀ ምጡ?
ብዬ ...
ራሴን በጀርባዬ አዝዬ
እጄን ከ'ጇ ጣል ባረገው
ደስታዋን አጠወለገው።
ክሰል ገላዋም ተናደ
ከተፋኝ ጥልቀት ተዋሀደ
ታሪካችንን አፈር አልብሳ
ዳግም በቀለች ሙት አፈር ልሳ።

.
.
.
ይለጥቃል . . .
.
.
.

ካኖርንበት ስናነሳ...
.
.
.
ሄዶን

#ገፅ አምስት
የጠፋው ገፅ

የስንብት ቃል

እንደ ቅርበትሽ ባልፀና
ነበር ጎትቶ ቢያርቀኝ
ቃላት ሸሽተው ከምላሴ
ዝምዝምታው ልቆ ቢቀለኝ
ለመራቄ የሚያዋጣ
ፍቅርሽ ውስጤ ነበረኝ።
#ስሞታ


#ገፅ አልባ አንድ እውነት

አድባሬ ናት ብዬ በምልልስ ብሞግታት፡ ቅንዝር ምንዝር ልኩን ላያልፍ ፡ ቀኑን ጠብቆ መንግስቴ ወደቀ። ዘውዴን ወዲያ አሽቀንጥሬ ልማድ ላ'ድን ወደ ማላውቀው ወደማያውቀኝ ኮበለልኩ ፤ ራቅኳት ብዬ ከራቅኩበት ሳለሁ ዓይኔ መሀል እስካገኛት፡ የሌለሁባት የሌለችብኝ ይመስለኝ ነበር።

#ዓይኔ ዓይኑ ሆና

ቅጥሩ ተንዶ
የመሸገበት ሲጋለጥ ዱሩ
ዘመን ያፀናው ላልቷል ጉንጉኑ
ዓያት ስታየው ዓይኔ ዓይኑ መሀል
የፅልመት በትር ሆና ብሌኑ።


= ከገዛ ገላዬ ከመዳራት ባ'ማልክቱ እርዳታ አመለጥኩ። አቤቱ አንድያ ዓይኔን ጠብቅልኝ። በእርሱ ህልውና ነውና ብሌኑም፤ ትርጉሜም ነፍሳቸው ህያው ሆኖ የሚቀጥል።

የአማልክቱ በረከት ይደርብን!!
አሜን!


የልደት ስጦታ!
Ⓒhedon2022
630 viewsBell, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 07:37:33 ለእናቶቻችሁ ወይም ለባለቤቶቻችሁ ስሜታችሁን ለመግለጽ በዚህ ፃፉልኝ እለቀዋለዉ

@semirmotivation
658 viewsسمير ايمي, 04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 22:45:35 ☞ ዝክረ ኸሚስ 6
.
የሩቅ እንጉርጉሮ
።።።።።።።።።።።።።
ሰው በመሆን ንጋት ፣
ሰው በመሆን መንገድ
በሓድራ አደባባይ ላ‘ብሮነቱ ሰንደቅ ፣
ሰው የማለት ዜማ በመሀባ ቅኝት ቃሉ ሲንደቀደቅ ፣
( ፍቅር ምን ይመስላል ... ! )
የኔነትን ዋርካ ... ላብሮነት መገንደስ ?!
ክፋት ግብግቡን ...ጥል መሻቱን መዳስ ?!
.
በኒያ ኮርቻ ፣
በጡሀራ ልጓም ፣
የከራማውን ኩል በሂማ ወለባ ጀማው ጋራ ኩለው ፣
ቼ በለው ለሀገር - የመኣና ፈረስ በጀዝም ኮልኩለው፣
( እንደምን ነው መድረስ ... ! )
የኽልቄውን ሃጃ ... በአማና ማድረስ ?!
ያገሬውን ሰማይ ... ለ‘ርዚቅ መኸር ማረስ ?!
.
እኮ ...
( ፍቅር ምን ይመስላል ... !? )
( እንደምን ነው መድረስ ... !? )
.
ሃያማ ንገሩኝ ...
የቀን መቅናት መልኩ ... መጠኑ ቀለሙ ?!
ከአዚማም ግርዶሽ እራሱን ፈልቅቆ ንቃት መሸለሙ ?!
.
ሃያማ ንገሩኝ ፣
ላለማዝመም ማግሩኝ ።
.
ድንግር ባለው ልብ ፣
ብትል ባለው ቀልብ ፣
በኢማን ድግ ሊያስሩት ፣
እንደት ነው መሰተር ... ጥመት ሲንጨፈረር ፣
ነፍሴ እንደት ይመይዝ ... ለጋ አቅሌ እንዴት ይክረር ?
.
« ሓድራ አደባባይ ሁሉም ይታጫል ፣
ያገር ልጅ ሲቀር እንደት ይቆጫል ። »
.
ብላችሁስ የለ !
.
ብቻ ባለሁበት ...
.
« ያ‘ብሮነት ድልድዩ
መሀባ እያረጀ ሽበቱ ወረረው ፣
አንድ ሰው ብቻውን ይሻገር ጀመረው ። »
.
አዎ ... !
ይሄው ነው አውነቱ ።
.
ዛሬ‘ኔ እንደዋዛ ...
ዘመንን ስናፍቅ ፣
ስስት ምቹ መቶኝ ፣
አቅሌ ሲጉረበረብ ፣
እሞዠርግበት ቀልቤ ጥፍር የለው በላኝ እንዳብላሊት፣
ያጎረፋችሁት አባይ ገላው ኸይሚስ ሽርጥ ሲል ለሊት።
.
.
እንጂማ ...
ምን የሞቀ ጠሀይ ... ምን የሰባ ጀንበር ፣
ምን ኣጀብ ጨረቃ ... ምን የኮከብ ገበር ፣
ምን የበለገ እጣ ... ምን የሞላው መክበር ፣
( ምን ያማረን ዘመን ... ! )
የቀልብ መሰላል ማማውን ማግሬ ፣
በሩቁ መነጠር - በዘማች መስታዎት ባየው አሻግሬ፣
ጉድ በል ነው ...
ነፍስያን እንደ ጨርቅ ፣
ከመናቀፍ እድፍ እያንጨፈጨፈ ...
ምን ያጥበውን አቅል ... ምን ያለዝብን መንፈስ ፣
የመሀባው ጂረት ሰውነት ወጅሮ ይታየኛል ሲፈስ ።
.
እንጂማ ይታያል ይዳሰሳል ፍቅር !
እንጂማ ይሠማል ይደመጣል ፍቅር !
ሁሉም እንደ ልኩ ...
እውነት ሲከፋፈል ... ውብ ቃሉ ሲፈሰር !
.
እንጂማ ይነካል ...
ገምሻራው አካሉ ፍቅር ይዳሰሳል !
እንጂማ ያለዝባል ወንዝ ነው ይፈሳል !
( ሌት አለው ውብ ዜማ ...
በሩቅ አብሰልስሎ የራስ እንጉርጉሮ ከራስ የሚቀማ።)
_
Semir aklu
837 viewsسمير ايمي, 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 22:57:35 ለውብ ለይል ቅዳሜ


semir aklu

The magic of thinking BIG!!!!


( ሂማ አታሳንሱ!!!!!!!)

@ መግቢያ፣ ሂማ በአረብኛ ይሆንልኛል ብለን የምናስበው፣ ራእይ፣ ምኞት፣ ሃሳብ
የምንፈጽምበት ትልቅ ወኔ ጭምር ማለት ነው።
ሰሞኑን The magic of thinking BIG!!!! በሚል ርእስ የተፃፈ አንድ የፈረንጅ ሃገር
መፅሃፍ እጄ ገባና ሳነበው ከረምኩ። አነቃቂና አደፋፋሪ መፅሃፍ ነው። በትልቁ እያሰቡ ፣
በትልቁ እያለሙ ፣በትልቁ እየሰሩ መኖር ለሰው የተሰጠው ፀጋ ነው፣ ለሰማይ ያሰቡት ጣራ ሳይነካ አይመለስም፣ ለተራራ ያለመ ኮረብታውን መነቅነቁ አይቀርም ይለናል። ከሰራነው
ታላቅ ታሪክ ይልቅ ገና የምንሰራው ታሪክ ይበልጣልና ዛሬ በዙሪያችን የተሰጠንን ትንሽ እድል በግዙፍ ራእይ አጅበን ትልቅ ታሪክ እንሰራበት ዘንድ አበክሮ ይመክራል። ፈጣሪ በውስጣችን ያስቀመጠው አቅም ተአምር ለመስራት አይገደውምና በምናየው ገደብ
ከመታሰር ይልቅ ተግዳሮቱ በውስጣችን ከተሸሸገው ቅምጥ አቅም ( potential) አንፃር ሲታይ ኢምንት ነውና በትልቁ እያለምን፣ በትልቁ እያሰብን ፣ ለትልቅ ታሪክ እንተጋ ዘንድ ወደፊት በሉለት ይለይለት እያለ ወደ ስኬት ዘመቻ ይመራናል።

በመፅሃፉ ውስጥ የተቀናበሩትን እሳቤዎች አብዝቼ ባሰብኳቸው ግዜ ከገዛ ዘመዶቼ ጓዳ ከዘመን በፊት ሲነገር የቆየ አንድ ትርክት ወደ ማእደ ትውስታዬ ተዘረጋልኝ። እንዲህ ነው ነገሩ። ባንድ ወቅት አንድ ከራማ ሞልቶ የሚፈስባቸው ትልቅ ሼክ ነበሩ እየተባለ ይነገራል።
ዱኣቸው ቅቡል የሆነ፣ ምርቃታቸው ገና ከአፋቸው ሳይወጣ የሚደርስ፣ በቱፍታቸው በሽታ የሚያሽሩ ነበሩ ተብሎ ይተረክላቸዋል። ብዙ ዘመን ሚስት ያገቡ ዘንድ ተለምነው ተለምነው " እምቢኝ ገና ነው የኔ ሰርግ" እያሉ ይመልሱ ነበር። ባንድ ወቅት የቤት ጉዳያቸውን የምታከናውን የቤት ሰራተኛ ( ካዳሚ) ወደ ቤታቸው አመጡላቸው። ጠንካራ፣ስራ ወዳድ፣ ተንከባካቢ ሴት ሆነችላቸው። እነ ሼህ ቅዳሜ ቅዳሜ ዱኣ አያልፋቸውም። ባንድ ቅዳሜ ቀጤማው ተነስንሶ፣ ሳሩ ተጎዝጉዞ፣ እረከቦቱ ተሰይሞ ሳለ
የነፍስያቸው መቃኛ የሆነውን የዱኣ ላይ እንጉርጉሮ በሸገነው ድምፃቸው ያወርዱት ጀመር። እንጉርጉሯቸው ለቀዬው ሰው ሁላ ማነቃቂያ፣ ለካዳሚዋ ሴት ደግሞ በየሳምንቱ እየተናፈቀ የሚመጣ በረካ ነው። ካዳሚዋ ሴት የእነ ሸህን እንጉርጉሮ በሰማች ግዜ ነፍሷ ጥፍት ይላል። ድምፃቸውን በሰማች ግዜ ልቧ ይሸፍታል። ስኒው ከእጇ ያመልጣል፣ ጀበናው ገንፍሎ ይኩረፈረፋል፣ ይህ ሁሉ ሲሆን እሷ ግን በአድናቆት ተመስጣ የነሸህን አይን አይናቸውን እያየች አለሙን ሁሉ ትረሳለች። ወደ ዃላ ላይ አድናቆት ወደፍቅር ከፍ ብሎ ተቸገረች። ፍቅር እንደለከፋት አይነውሃዋ ያሳብቅባታል። ይህንን እውነታ ሼሁ በዘወርዋራ
መንገድ አወቁት። ""።ይህች አቅሟን የማታውቅ ሴት እኔን መመኘቷ አሳቀኝም፣
አሳቀቀኝም"" እያሉ ከራሳቸው ጋር ሲያወጉ ከረሙ። ታዲያ አንድ ቅዳሜ የዱኣው ሃድራ በሞቀበት፣ ካዳሚዋ ሴት ቡና እያፈላች ሳለ እነ ሸህ ማንጎራጎር ጀመሩ። በቅኔ ተስፋሊያስቆርጧት ፈልገው ኖሮ እንዲህ ሲሉ ተቀኙ።


እሳት ነዶ ነዶ፣ ሰማዩን አይፈጅም፣
የማያገኙትን፣ መከጀል አይበጅም።


ይህን የሰማችው ካዳሚ እንዲህ መለሰችላቸው።

እሳት ምድር ነዶ፣ ሰማይ ላይ ነው ጭሱ፣
አምላክ ለሚያደርገው፣ ሂማ አታሳንሱ።

እነ ሸህ ይህንን መብረቅ የሆነ መልስ ሲሰሙ ተብረከረኩ። የልጅቱ ብርታትና የልብአፍቃሪነቷ አሸነፋቸው። ቡናው እየተቀዳ ሳለ እንግዲህ ሚስቴ አንችው ነሽ ብለው በወግ በማረግ ተዳሩ።
አያችሁ እነ ሼህ እንዴት የቤት ሰራተኛዬ ጌታዋን ልታገባ ሽቅብ ትመኛለች?? ብለውአሰቡ። ዋናው ምስጢር ያለው ልብ ላይ ነው። ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚሁ ይሆናል።የቤት ሰራተኛ ተብላ ብትጠራም እሷ ግን ራስዋን እንደ እቴጌ ቆጥራ ነው የኖረችው። ሃገር መንደሩ እንደ ገረድ አድርጎ ቢጥላትም እሷ ግን የእነ ሼህ ማጀት ባለ ሙሉ ሹመኛ እመቤት አድርጋ ነበር ያሰበችው። ለትንሽ ስራ ተጠራች እሷ ግን በትልቁ አሰበች እናም ባለ ትልቅ ህልም ሆና ሃሳቧን አሳካች። ከዚህ ወዲያ The magic of thinking BIG!!!!
ይኖራል እንዴ???? የኛ ዘመዶች ከፈረንጆቹ በፊት አቅምና ጉልበት የሚሆን ሃገርኛ ፍልስፍናነበራቸው ማለት ይሆን????

#አንድ ታሪክ ደግሞ ከባህር ማዶ እንጨምር


ቦክሰኛው መሀመድ አሊ ቴሬልን ለመግጠም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ቴሬል በድሮ ስሙ ካሲስ ክለይ እያለ ሲጠራው ለምን በባርነት የነጭ ስም ትጠራኛለህ በስሜ "መሀመድ" ለምን አትለኝም? ቢለውም ቴሬል "መሀመድ" ላለማለት "ክለይ" እያለ እምቢ በማለቱ ግብግብ ተፈጠረ። በ ቦክሱ ግጥሚያ ቀን መሀመድ አሊ ከሰባተኛው ዙር በኋላ እየቀጠቀጠው "ስሜ ማን ነው" (What is my name) እያለ ይጮህ ነበር። መሀመድ አሊ በቦክስ አለም እንዲህ ሲናደድ ታይቶ አይታወቅም። መጨረሻ ላይ ምን እንደተፈጠረ HBO በዚህ ጉዳይ documantary ሰርቶበታል በአጭሩ ግን ይህንን ተመልከቱ። ራስህን ሁን ራስህን አስከብር አትሽለጥለጥ።
**
ሸንበ
ቆ ቢረዝም ቅል አያንጠለጥልም
ሂማ የሌለው ሰው ቢታገል አይጥልም


እውነትም ሂማ አታሳንሱ!!!!!!!!!!
976 viewsسمير ايمي, 19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 08:55:09 ሕያው

ከሰራነው ንጣፍ..


ርቀት ፀንቶ ላይቆም በራሱ እያመነ
ክፍተት ባንቺ ገላ እየተሸፈነ

ጥግት..

ፍርሀት እጅ ሰ'ቶ
የኔና አንቺ ክንዶች ነፃነት ቀንቷቸው አንዱ ባንደኛው ላይ
ስህበት ድል ነስቶ ከጥጋታችን ውስጥ ነፋስ መውጫ ላላይ

እቅፍ..

በእቅፋታችን ስልት በላብ ወዝ መጣበቅ መላቀቅን መናቅ
በዕምነት ልክ ማየት አንድ ሌሊት መኖር እልፍ ነገን ሳናቅ

ጥብቅ..

አንድ መሆን አይነት ያንቺን ትንፋሽ መማግ ውስጥሽን መተንፈስ
ያንቺን ህልም ማለም መኖር ያንቺን መንፈስ

ዋህድ..

ሌላ ገፅ ውህደት መዳፌ ካካልሽ ወደ ልብሽ ግድም
እንዲህ ባ'ለ ውበት የተኖረ ምሽት ቢነጋም አይገድም።

ጥፍትት..

@merekkk




╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza
835 viewsBell, edited  05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:07:10 ወድቆ በመነሳት
ያለፈን በመርሳት
ለፍቅር መረታት

ሀዘን ብሎ ፌሽታ
በናፍቆት ስቅታ
ባለፈው ትውስታ

 እየተፅናናን

በመልካም ልቦና
በአምላክ ምስጋና
ሂወት ስትቀና

ሁሉን አሳልፎ
የበላነው ተርፎ
የሰራነው ገዝፎ
ከፍታን ይዘናል
ፍቅር ሰንቀናል
ባለፈው አመት ላይ እድገት ጨምረናል፡፡
.

Semir ami


Artot
978 viewsسمير ايمي, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 23:43:26 ሄዶን

_የትዕንግርት ፍሬ_

አጠርጥር ድባቴን
ከፍተህ ግባ ቤቴን

እምጥ ባይደላ ስምጥ
ዱካህን አስቀምጥ

ሀቄን ናፍቀህ አትሠደድ
ንፉግ ጭርታዬን ልመድ
ረብ አደንህ ለስጦታ
ርቆ ላይሠጥ ለኔ ደንታ
ቀርቦ ላይንድ ነበር ቦታ
አታድክመኝ ባ'ጉል ድካም
በመስዋዕት እኔ አልረካም።

ፅኑ መሻቴን ሸክፌ
ዘመኔን በሩጫ አልፌ
ብደናበር በድንግዝግዝ
በሙከራ ላላረግዝ
ከዝብዘባህ ድንገት ስቶ
ቅፅበት ሀቁን መራኝ እንጂ
ለድረታህ አልባክንም
ልቤም ሽፍታ እግሬም ሀጂ።

ምናልባት እዛጋ

ባይተዋር ተማፅኖ ጩኸቴን ሲጠጋ
ፈሪ አማኝነትህ በቃሌ ባይረጋ
የት'ንግርትህ ፍሬ መሆኔን አትዘንጋ።

መረቅ
@merekkk



╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza
896 viewsBell, 20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 14:48:48 #ሸሸግ_በል !
/
ያኔ ...
በሙሉ አቅምህ ስታበራ
ያለህን ሳትሰስት ስትዘራ፣
ተጣድፎ - ከንፎ ያለፈህ
ዘርግቶ ድባብ ዣንጥላ
ከጮራህ ሽሽት ከለላ፣...
-
ዛሬ በቀን - በጊዜ አዋጅ
በአልፎ ሃጅ - በተራማጅ፣
ስትሸፈን - ስትከለል
በገላህ ላይ ሽርጥ ሲጣል፣...
-
በዚያች ዕድሜ፣
በዚያች ትንፋሽ፣
ይ ጀ ም ራ ል ያንተ ተውኔት
የዘላለም ጣፋጭ ቅፅበት!!
-
ይ ነ ጠ ፋ ል! ...
ይ ዘ ረ ጋ ል! ...
ሞልቶ ይፈ'ሳል ...!
በዚያ ፈለግ - በዚያ መንገድ
የሰው ፍቅር - የሰው መውደድ፨
----------------//------------------
( semir ami
778 viewsسمير ايمي, 11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ