Get Mystery Box with random crypto!

ሄዶን _የትዕንግርት ፍሬ_ አጠርጥር ድባቴን ከፍተህ ግባ ቤቴን እምጥ ባይደላ ስምጥ ዱካህን አ | ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

ሄዶን

_የትዕንግርት ፍሬ_

አጠርጥር ድባቴን
ከፍተህ ግባ ቤቴን

እምጥ ባይደላ ስምጥ
ዱካህን አስቀምጥ

ሀቄን ናፍቀህ አትሠደድ
ንፉግ ጭርታዬን ልመድ
ረብ አደንህ ለስጦታ
ርቆ ላይሠጥ ለኔ ደንታ
ቀርቦ ላይንድ ነበር ቦታ
አታድክመኝ ባ'ጉል ድካም
በመስዋዕት እኔ አልረካም።

ፅኑ መሻቴን ሸክፌ
ዘመኔን በሩጫ አልፌ
ብደናበር በድንግዝግዝ
በሙከራ ላላረግዝ
ከዝብዘባህ ድንገት ስቶ
ቅፅበት ሀቁን መራኝ እንጂ
ለድረታህ አልባክንም
ልቤም ሽፍታ እግሬም ሀጂ።

ምናልባት እዛጋ

ባይተዋር ተማፅኖ ጩኸቴን ሲጠጋ
ፈሪ አማኝነትህ በቃሌ ባይረጋ
የት'ንግርትህ ፍሬ መሆኔን አትዘንጋ።

መረቅ
@merekkk



╔═══❖• •❖═══╗
@faiza_kiza
╚═══❖• •❖═══╝

For any comment
@mornin_bot
❥❥__⚘_❥❥

Share


Join @faiza_kiza