Get Mystery Box with random crypto!

#ሸሸግ_በል ! / ያኔ ... በሙሉ አቅምህ ስታበራ ያለህን ሳትሰስት ስትዘራ፣ ተጣድፎ - ከንፎ ያ | ፅሁፍ በፋኢዛ 🤗

#ሸሸግ_በል !
/
ያኔ ...
በሙሉ አቅምህ ስታበራ
ያለህን ሳትሰስት ስትዘራ፣
ተጣድፎ - ከንፎ ያለፈህ
ዘርግቶ ድባብ ዣንጥላ
ከጮራህ ሽሽት ከለላ፣...
-
ዛሬ በቀን - በጊዜ አዋጅ
በአልፎ ሃጅ - በተራማጅ፣
ስትሸፈን - ስትከለል
በገላህ ላይ ሽርጥ ሲጣል፣...
-
በዚያች ዕድሜ፣
በዚያች ትንፋሽ፣
ይ ጀ ም ራ ል ያንተ ተውኔት
የዘላለም ጣፋጭ ቅፅበት!!
-
ይ ነ ጠ ፋ ል! ...
ይ ዘ ረ ጋ ል! ...
ሞልቶ ይፈ'ሳል ...!
በዚያ ፈለግ - በዚያ መንገድ
የሰው ፍቅር - የሰው መውደድ፨
----------------//------------------
( semir ami