Get Mystery Box with random crypto!

#የመሬት_መዋቅር_ምን_ይመስላል? መሬት በመዋቅሯ ከእንቁላል ጋር ተመሳሳይ መዋቅር አላት፡፡ ውስጣ | ጠቅላላ እውቀት

#የመሬት_መዋቅር_ምን_ይመስላል?

መሬት በመዋቅሯ ከእንቁላል ጋር ተመሳሳይ መዋቅር አላት፡፡ ውስጣዊ እና ውጫዊ ይዘቷ በአጠቃላይ በሶስት ይከፈላል፡፡ ይህም በእንቁላል አካል የውጨኛው ቅርፊት፣ የመካከለኛው ፈሳሽ እና የውስጠኛው አስኳል ብለን እንደምንከፍለው በመሬትም ተመሳሳይ አቀማመጥ ያላቸው ክፍሎች አሉ፡፡

ውጫዊ ክፍል

የመጀመሪያው ውጫዊው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ክረስት የሚባለው ሲሆን የመሬት ቅርፊት ልንለው እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ከተለያዩ የቋጥኝ አይነቶች የተገነባ ሲሆን ህይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ የሚኖሩት በዚህኛው የመሬት ክፍል ላይ ነው፡፡ ይህ ክፍል ውፍረቱን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በውቅያኖሶች ስር ያለው የውፍረቱ መጠን እና በአህጉራት ላይ ያለው መጠን ስለሚለያይ ነው፡፡ የመሬት ቅርፊት በውቅያኖሶች ስር ያለው ውፍረት ከ5000 ሜትር እስከ 10000 ሜትር ነው፡፡ ይህ ውፍረት በአህጉሮች ላይ ከ30 ኪ.ሜ እስከ 50 ኪ.ሜ ነው፡፡

መካከለኛው ክፍል

ሁለተኛው የመሬት ክፍል መካከለኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ማንትል በመባል ይጠራል፡፡ ይህ የመሬት ክፍል ፈሳሻማ ይዘት አለው፡፡ ውፍረቱ እስከ 2890 ኪ.ሜ ይደርሳል፡፡ የመሬትን 84 በመቶ መጠን ይሆናል፡፡ በአብዛኛው በቅልጥ አለት ወይም ማግማ የተሞላ ነው፡፡

ውስጠኛው የመሬት ክፍል

የመጨረሻው እና ሶስተኛው ደግሞ ውስጠኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ኮር የሚባለው ነው፡፡ በእንቁላል የውስጠኛው አስኳል መወከል ይቻላል፡፡ እጅግ በጣም ሞቃት ሲሆን የፀሐይን የውጨኛ ክፍል መጠነ ሙቀት ይኖርዋል፡፡ ይህ ክፍል መጠኑ አነስተኛ ሲሆን በራዲየስ እስከ 1220 ኪ.ሜ ብቻ ነው፡፡ በዚህም የጨረቃን መጠን 70 በመቶ ጋር ይነጻጸራል፡፡

@ewentesfa @ewentesfa