Get Mystery Box with random crypto!

የአውቶማቲክ መኪናን ጊርቦክስ ሊያበላሹ የሚችሉ ቀላል የሚመስሉ ነገር ግን አደገኛ የሆኑ 5 ስ | ጠቅላላ እውቀት

የአውቶማቲክ መኪናን ጊርቦክስ ሊያበላሹ የሚችሉ ቀላል የሚመስሉ ነገር ግን አደገኛ የሆኑ 5 ስህተቶች!!

➊ D ላይ ሆኖ እየተነዳ ያለን መኪና ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴውን በ ፍሬን ሳያቆሙ ወደ ሗላ ለመሄድ R ማስገባት::

➋ ነዳጅ ለመቆጠብ ተብሎ ቁልቁለት ላይ መኪናውን በ N መልቀቅ::ይህ ድርጊት አሽከርካሪው መኪናውን መቆጣጠር እንዳይችል በማድረግ እንዲሁም የመኪናውን የማርሽ ታይሚንግ ዙር ሲንኮራይዚንግ በማዛባት ለ አደጋ ያጋልጣል::

➌ በ እንቅስቃሴ ላይ ያለን መኪና በቅድሚያ በፍሬን ሳያቆሙ P ማስገባት ::

➍ በረጃጅም የመንገድ መጨናነቅ (ረጅም ሠልፍ) ወቅት መኪናችንን D አድርጐ አለመጠበቅ ምክንያቱም ለከፍተኛ ሙቀት overheating ስለሚያጋልጠው በተቻለ አቅም p ላይ አድርገን መጠበቅ ተመራጭ ነው::

➎ መኪናችን N እንዳለ ከፍተኛ ነዳጅ ሰጥቶ በቀጥታ ወደ D ማስገባት ይህ የአውቶማቲክ ጥርሶችን በአንድ ጊዜ ከጥቅም ውጪ ያረጋቸዋል

➹share &Join Us

               @ewentesfa