#ስኳር_በሽታ_ላለባቸው_ሰዎች_8_ምርጥ_ምግቦች
1. ገብስ:- ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።
2. ባቄላ እና ዘሮቹ:- ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
3. እንቁላል(በመጠኑ):- እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።
4. አሳ:- የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።
@ewentesfa @ewentesfa