Get Mystery Box with random crypto!

ከመገፋት የተገፋ (ብንያም ወጋየሁ) . . ከመምጣት ለካ መሄድ ይቀላል ካንቺ ተኳርፎም እራስ | ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

ከመገፋት የተገፋ
(ብንያም ወጋየሁ)
.
.
ከመምጣት ለካ መሄድ ይቀላል
ካንቺ ተኳርፎም እራስ ያስጥላል
መገፋት ስንት ነው
አቅሙስ የፍቅርን ብርታት ያህላል?
ለንደኔ አይነት ሰው
ከመገፋት የተገፋ
ከመከፋት የተከፋ
ምን ፍቺ አለው ምንድን ተስፋ?
አንድ ማግኘት
ሁለት መመኘት
አንድ እኔ አንድ አንቺን መሰኘት
አንድ ማጣት
ሁለት ቅጣት
ከአንድ እኔ ከአንድ አንቺ መታጣት
የእንባ ትርጉም
ላንቺ ፍቺው የስላቅ ጉም
ከራስ ለተጣጣው
በፍቅር ለተቀጣው
ከመገፋት መንገድ ቀኔ አስሮኝ መጣው
(ፍቺኝ)
የፍቅር ጉልበት በአቅም አይረታም
ልክ እንዳንቺ
የታሰረን ገላ
አሳሪው ነው እንጂ ሌላው ስም አይፈታም
እንደሰው ያለ ከወዴት ይገኛል
ቆስሎም ደምቶም አሳሪውን ይመኛል
ከነፍስ ከመንፈስ ስጋ ሁሌ ይፋታል
በመገፋት ያለ በፍቅር ይረታል
በዚች የከፋች ከንቱ አለም
ማፍቀር እንጂ መግፋት ብርቅ አይደለም
ከዘላለማችን አኳርፎ
እርኩሰት አይቀመጥ አርፎ
እንኑር አብረን
ዘመን ይብራልን ገዝፎ
ዛሬም
ከመገፋቴ የሚገፋኝን አሳሪዬን እመኛለው
(ለአሳሪ
ከመፋቀር ባህር
ገብቶ መሰዋት አስባለው።
( .. ፍቺኝ..)
@yotorr