Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ etyokenaandkald — ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ etyokenaandkald — ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ
የሰርጥ አድራሻ: @etyokenaandkald
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 191
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም ፣ ቅኔእና ቀልድየሚለቀቅበት ቻናል ነው
የሚለቀቅ ግጥም እና ቅኔ ካሎት እና እዚህ ላይ አናግሩን

👇👇👇👇👇
👉 @ethio_kene👈
👆👆👆👆👆
ለአድ ሚን በዚ ላይ አናግሩን
@eyobnagn

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-19 20:37:46 እንጀራ ፊትሽን እያየው በህልሜ
እቤትሽ መጣውኝ ወጡን ተሸክሜ
192 views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 20:37:46 ውሻ ይደነፋል በአንበሳ ጓሮ
ደቦሉ ሲመጣ ሊሮጥ ደንብሮ
182 views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 20:37:46 እንጀራ ፊትሽን እያየው በህልሜ
እቤትሽ መጣውኝ ወጡን ተሸክሜ
176 views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 20:37:46 ውሻ ይደነፋል በአንበሳ ጓሮ
ደቦሉ ሲመጣ ሊሮጥ ደንብሮ
176 views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-18 09:07:15 (ብንያም ወጋየሁ)
የደግ ቅናት
..
.
ታውቂያለሽ
የኛን ነገር ሳስብ ሌሎችን አያለው
በሌሎች ቀናለው
ማን ነበረን እስኪ ከኛ ውጪ መቅድም?
ማለት ለምንድነው
አንቺን ለኔ አድርጎ ከፈጠረሽ ኋላ ፈጣሪ አይፈቅድም
ባይገባሽ ነው እንጂ
ፈጣሪ አይፈቅድም ብለሽ ያማረርሽው
ምን ያደርጋል መፍቀድ
እሱ እሺ ብሎ አንቺ እንቢ ካልሽው
ሰው የሚሉት ፍጡር ፍቅርን የገፋ ለት
ፍቅርን ገፋ ማለት
ኢ-ምንት አልቦ አድርገኝ ብሎ መግባት ስለት
ማነው የተሳለው?
ከሰውነት ገደብ እንነቀል ያለው
ለዚህ ነው
የምቀናው ባንቺ ስትመጪ ስትሄጂ
አይምሰልሽ ሐራም ቀና ቅናት እንጂ
አዎን እቀናለው
ያልቀኑበት ነገር አልቦነት ስላለው
ባንቺ...ቀንቻለው

ለካ በህይወት ውስጥ ሲ'ኖር በዚህ አለም
የኛን የሚያይልን ሌላ ዳኛ የለም።
(መቅናት ክፉ አይደለም)
@yotorr
178 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 23:40:34 ከመገፋት የተገፋ
(ብንያም ወጋየሁ)
.
.
ከመምጣት ለካ መሄድ ይቀላል
ካንቺ ተኳርፎም እራስ ያስጥላል
መገፋት ስንት ነው
አቅሙስ የፍቅርን ብርታት ያህላል?
ለንደኔ አይነት ሰው
ከመገፋት የተገፋ
ከመከፋት የተከፋ
ምን ፍቺ አለው ምንድን ተስፋ?
አንድ ማግኘት
ሁለት መመኘት
አንድ እኔ አንድ አንቺን መሰኘት
አንድ ማጣት
ሁለት ቅጣት
ከአንድ እኔ ከአንድ አንቺ መታጣት
የእንባ ትርጉም
ላንቺ ፍቺው የስላቅ ጉም
ከራስ ለተጣጣው
በፍቅር ለተቀጣው
ከመገፋት መንገድ ቀኔ አስሮኝ መጣው
(ፍቺኝ)
የፍቅር ጉልበት በአቅም አይረታም
ልክ እንዳንቺ
የታሰረን ገላ
አሳሪው ነው እንጂ ሌላው ስም አይፈታም
እንደሰው ያለ ከወዴት ይገኛል
ቆስሎም ደምቶም አሳሪውን ይመኛል
ከነፍስ ከመንፈስ ስጋ ሁሌ ይፋታል
በመገፋት ያለ በፍቅር ይረታል
በዚች የከፋች ከንቱ አለም
ማፍቀር እንጂ መግፋት ብርቅ አይደለም
ከዘላለማችን አኳርፎ
እርኩሰት አይቀመጥ አርፎ
እንኑር አብረን
ዘመን ይብራልን ገዝፎ
ዛሬም
ከመገፋቴ የሚገፋኝን አሳሪዬን እመኛለው
(ለአሳሪ
ከመፋቀር ባህር
ገብቶ መሰዋት አስባለው።
( .. ፍቺኝ..)
@yotorr
172 views20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 21:43:59 ተስፋሽን ፈራሁት (በድሉ ዋቅጅራ)

የደጅሽ አበባ፣ እምቡጥ ሲይዝልሽ፤
የታቀፍሽው ህጻን፣ ጠብቶ ሲያገሳልሽ፤
ደስታሽን አይቼ፤
ተስፋሽን ቃኝቼ፤
. . . . . .ነገሽን ፈራሁት፡፡

እምቡጥ የሚያመክን፣
አመዳይ
ትላትል
ተምች በሞላበት፤
እንቡጥ የሚቀጥፍ፣
ሰው በሚኖርበት፤
. . . . . . . . . በእኔና አንቺ አለም፤
ማንቦጥ መታጨት ነው፣
መውለድ መከተብ ነው፣
የዘላለም ሀዘን፣ የዘላለም ህመም፡፡
-------------
(የተስፋ ክትባት )
@kene_tobeya
161 views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 21:22:21
ያገሬ ሰው አብዷል
ህዝቤ ጨርቁን ቀዷል
ወይም እኔ እብድ ነኝ ከሰው የተለየሁ
ይኸው አሁን እንኳን
አዳነች ይሉኛል ስትገድል እያየሁ

[ ደሱ ፍቅሬል ]
173 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 14:26:16 "ያላለቀ ግጥም"
(ቢኒያም ወጋየሁ)
.
.
ታስታውሺው እንደው
ያኔ አብረን ሳለን
አለም ሁሉ ሰፍቶን
ሀገር ሁሉ ደልቶን
ከመፋቀር ባህር እንደተቀመጥን
የሆነ ጊዜ ላይ
ከእግረ ሙቅ ተላቀን ከፍቅር ያመለጥን
... ነበርን...
በሰራውት አለም በሰራሽው አለም
ለኛ የማይበቃ አንዳች ተዐምር የለም
(ይኸው ለኔና አንቺ ተዐምር ብርቅ አይደለም)
አንቺን የማጣቴ እልፍ ቀን ቢመጣም
ዛሬም ከአንደበቴ
ተለየሺኝ የሚል አንዳች ቃል አልወጣም
ብትሄጂም ብትርቂም
መንገድን ብታውቂም
ብትራመጂኝም
... አልተለየሺኝም...
እውነት ነው
እልፍ ተዐምር አለ አብረን የሰራነው
እውነት ነው
እልፍ ታሪክ አለ ስንቀምር የኖርነው
እልፍ ቀኖች አሉ እኛን የሚገሉን
እኛን የሚያኖሩን እልፍ"እልፎች"አሉን
... አልተለየሺኝም...
እኔ ጋር ልጅ አለሽ ብሶት የወለደው
እኔ ጋር "እኔ" አለሽ ፍቅር የገመደው.....
@yotorr
156 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 23:11:12 #እስኪ_እናስብ hafi nge በድጋሚ

አንድ የ 24 አመት ወጣት ከሚጓዝበት ባቡር አሻግሮ በሚያያቸዉ ነገሮች ተገርሟል፡፡ ከዛም ጮክ ብሎ "አባቴ ፥ ዛፎቹን እያቸዉማ ወደኀላ እየሆዱኮ ነዉ! " ሲለዉ አባትየዉ #ፈገግ አለ ፤ በቅርብ ያሉ ተሳፋሪዋች ግን የ 24 አመት ወጣቱን በሀዘን ስሜት እንደ ልጅና #ህመምተኛ ተመለከቱት፡፡
ወጣቱ በድንገት በመደነቅ ደግሞ "አባቴ ፥ ተመልከት ደመናዉ እኮ አብሮን እየሄደ ነዉ!" አለዉ፡፡ አባትየዉ አሁንም ልጁን #በፈገግታ ተመለከተዉ ፤ በቅርብ ያለ አንድ ሰዉዬ ግን ወጣቱ በሚያሳየዉ የልጅ ፀባይ አላስችል ብሎት በንዴት ...
"ለምን ልጅህን ወደ ጥሩ የአዕምሮ ሆስፒታል አትወስደዉም?" አለዉ ለወጣቱ አባት፡፡
አባትየዉ በአንዴ ፊቱ በሀዘን ተሞላ ፣ አይኖቹ እንባ እየተናነቀዉ በእርጋታ እንዲህ ብሎ መለሰለት..."ሆስፒታል ወስጄዋለሁ... ፥ አሁን ራሱ ከዛ እየተመለስን ነዉ ፥ ልጄ ከልጅነቱ ጀምሮ ማየት አይችልም ነበር ለወራት ከታከመ በኀላ ዛሬ ነዉ ታክሞ አይቶ ከሆስፒታል የወጣዉ" አለዉ ፡፡

#

በዚህ ምድር እያንዳንዱ ሰዉ የራሱ የሆነ ታሪክ አለዉ፡፡ የሰዉን ታረክ ሳናዉቅ ሰዉ ላይ ለመፍረድ አንቸኩል፡፡ ምክንያቱም እዉነታዉን ስንሰማና ስናዉቅ ሁሌ የተናገርነው ይቆጨናልና፡፡

#የሳምንት_ሰዉ_ይበለን
#ለሰዋች_የደስታ_ምንጭ_መሆን_ባንችል_የሀዘን_ምክንያት_አንሁን
#ፈጣሪ_ሀገራችንን_ይጠብቅልን_ሰላም_ያርግልን

ሀሳባችሁን በ @hafizy_25 አድርሱን
.
ቻናሉን ከወደዳችሁት ፤ አዲስ ሰለሆነ ሼር በማረግ እንድትተባበሩን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።
@hafila25 @hafila25 @hafila25
158 views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ