Get Mystery Box with random crypto!

አንሙት አብርሃም

የቴሌግራም ቻናል አርማ animutabraham — አንሙት አብርሃም
የቴሌግራም ቻናል አርማ animutabraham — አንሙት አብርሃም
የሰርጥ አድራሻ: @animutabraham
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.51K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-04 23:29:12
225 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 23:29:04 በዚህኛው እና ይሔን በመሠሉት አይደለም የክህደት እና ተቃርኖ መገለጫችን ይፋ የወጣው ፤

➙ በድሕረ-ደርግ የጀመረው የአማራ ቅራኔ፡ ከ2008 ጀምሮ በአዲስ ⁽⁽ማሕበራዊ ንቅናቄ⁾⁾ ሲመራ እና "የበለሳውን የአመራር ቡድን" ተጠያቂ ሲያደርግ፣ የበለሳዎቹ ስሪትና አስፈፃሚ የነበሩትን አድኃሪያን በለውጥ አመራርነት ሲቀበል ነው ተቃርኖው የጀመረው፤

➙ የአማራውን ⁽⁽ማሕበራዊ ንቅናቄ⁾⁾ በማጥቃት እና በማስጣል ሲሠሩ የነበሩ አመራሮች ፣ ድንገት የትግሉን ሚዛን ተከትለው ሲቀየሱ ፣ ያልፈጠረባቸውን እና የማያምኑበትን የአማራ ብሔርተኝነት ንቅናቄ ኮርጀው "ፊት መሪ" ሲመስሉና ሲደረጉ ነው ተቃርኖው የከፋው፤

➙ የአማራ ⁽⁽ማሕበራዊ ንቅናቄ⁾⁾ የጠበቀውን ውጤት እና ጥያቄዎቹን ለሌላ ጌታ አሳልፈው ሸጠው፣ ከሕዝቡ ጋር አብረው አልቃሽና ቆዛሚ ሆነው ሲሰለፉ ነው የሀሳብና አላማ ድርቅ ተቃርኖ፡ ፀሐይ የመታው፤

➙ ለ20 አመት እና ሰላሳ አመት ከአማራ መከራዎች ጎን ተሰልፈው የነበሩ ሰዎች፣ ይቅርታ ስለጠየቁ፡ የአማራ ጥያቄዎች እና ችግሮች መፍትሔ ይሆናሉ ተብሎ ሲገመት ነው የአማራ ውድቀትና ጥቃት ቀጣይነት የታወጀው፤

➙ በወታደራዊው መስክ፡ ለሩብ ክፍዘ የአማራ ወታደራዊ አባላትና አመራሮች ቅሬታ ሲያቀርቡ ፣ ሲባረሩ ፣ ሲነቀሉ እና ሲገፉ ያለእንቅፋት እስከ ሌተናንት ጀነራልነት የደረሰው አበባው ታደሰ ፣
የቅድመ-2010 ፖሊስ፡ የአማራ ልጆችን ሲያሳድድ፡ የተቋሙ ኃላፊ የነበረው ተመስገን ጥሩነህ ፣ ... ግለሰቦቹ ከመደበኛ ትምህርት ሪኮርድ ውስንነት በላይ፣
ያላቸውን "ውጫዊ ታማኝነት" እና "ፖለቲካ-አልቦነት" የዘነጋ ተስፋ ሲጣልባቸው ነው የአማራ ልጆች እሥራትና እንግልት ተቆርቋሪ አልባ መሆኑ ገሃድ የወጣው፤

➙ የአማራን ጥያቄ መመለስ አቅቷቸው ፣ ቆስለው አቁስለውን ፣ በመንደር ተሰልፈው እና በመንደር ተቧድነው፣ የግልና የመንደር አጀንዳ የፖለቲካ አላማ አድርገው ሕዝቡንም ለማባላት ሲሰለፉ ነው የአማራ ትግል መቀልበሱ ሌላ መልክ የያዘው ፤

➙ ወይ ለሰላም ወይ ለጦርነት ሳይዘጋጁ ፣ የአማራን ሕዝብ እጅግ አዋራጅ ለሆነ ጦርነት ዳርገውት ሲያበቁ፣ ለማያቋርጥ የጭፍጨፋ እና መፈናቀል ውርደት ዳርገውት ሲያበቁ፡ በስልጣን እና ገባሪነት እንዲቀጥሉ ሲፈቀድ ነው፡ የአማራ ፖለቲካዊ ውድቀቶች የተለየ ምዕራፍ የገቡት፤

➙ ስለሆነም፡ Sisay Awgichew Wondemtegegn (እና ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች) የሚንገላቱት፦

የኢሕአዴግ ሰልቫጆች በፖለቲካ ውድቀት ከፈጠሩት ጦርነት እና ውድቀት ይልቅ የተፈፀመን ግፍ በመፅሐፍ የመዘገበው ሲሳይ የሚወነጀለው ፣
እነሱ ማፈናቀሉን እና መጨፍጨፉን ማስቆም ይቅርና በተሰበሰቡበት ካምፕ ሊመለከቷቸው የሚጠየፏቸውን ተፈናቃዮች አለሁ በማለቱ የሚከሰሰው ሲሳይ፤
ዘጠኝ ዙር ያጠቁትን እና ያስጠቁትን አጣዬ መልሶ ለመገንባት በመሥራቱ የተወነጀለው ሲሳይ.... መነሻው ክህደትና ተቃርኖ ያጎበጠውን ፣ ግርድና የተለማመደውን፣ ብሔራዊ ስሜት የነጠፈበትን የብዐዴን ውራጅ በመሸከማችን ነው !!

መፍትሔውም ይሔንን አለቅት ከአማራ ትከሻ ፈጥፍጦ የሕግ ተጠያቂ ማድረግ ነው !!
224 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:45:39
ከመጋቢት እስከ መጋቢት!!

#የመጋቢትግፎች
#መጋቢት24
#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
463 views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:44:17
ከመጋቢት እስከ መጋቢት!!

#የመጋቢትግፎች
#መጋቢት24
#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
451 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:41:11
ከመጋቢት እስከ መጋቢት!!

#የመጋቢትግፎች
#መጋቢት24
#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
344 views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:40:46
ከመጋቢት እስከ መጋቢት!!

#የመጋቢትግፎች
#መጋቢት24
#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
342 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 08:40:36
ከመጋቢት እስከ መጋቢት!!

#የመጋቢትግፎች
#መጋቢት24
#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
311 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 06:47:13
ከመጋቢት እስከ መጋቢት!!

#የመጋቢትግፎች
#መጋቢት24
#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
351 views03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 05:44:39
ከትግራይ ጋር አንሶላ መጋፈፍ፣ የሚያሰጉ ክልሎችን መሳሪያ መግፈፍ!!

ጃዋር መሐመድ የሚባለው ፋሺስት ከትግራይ ጋር የሚደረግ ግንኙነት የስልጣናችን መጠበቂያ ነው ብሎ መክሮ ነበር።
⁽⁽በሻሻ አደረግናት ያሏት ትግራይ⁾⁾ እንዴት የስልጣን ዋስትና እንደምትሆን የምናየው ሆኖ፤ የወያኔን አንጀት አለማወቃቸው አስቂኝ የስልጣን ጥበቃ ሒደት አድርጎታል።

ቀደም ሲል የስርዓቱ ጉሮሮ አድርገው በአማራ ማንነት ሲያወድሷቸው የነበሩትን ወልቃይትና ራያ ፣ ⁽⁽ለአማራ ከተመለሱ የዲሞግራፊና ጆግራፊ አቅማቸው ስለሚጨምር ይገዳደሩናልና መመለስ የለባቸውም ፤ ከተመለሱ እኛም አዲስአበባን እንጠይቃለን⁾⁾ ሲሉ ነበር የባጁት።

እናም በወልቃይት ጉዳይ ከትግራይ ጋር መቆም አለብን የሚለው የኦነጋውያን አቋም የትግሬን ልብ ማለስለሻ ሆኖ ነው አንሶላ መጋፈፍ የተጀመረው።
የስርዓቱ አላዋቂዎች የSurvival strategy በብዙ ገፅታው ትራጄዲ ቢበዛውም፣ የኮሜዲ ክፍሉ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል የሚያሰኝ ነው።

#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
#የመጋቢትግፎች
#አማራያሸንፋል
#አማራ
367 views02:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 05:42:46 ⁽⁽የኦሮሞን ስልጣን ለማጠናከር እና ለመጠበቅ⁾⁾ ሲባል የሚወሰዱ እርምጃዎች ሁሉ አስቂኝም አሳቃቂም ሆነው ቀጥለዋል።

አሁን ደግሞ የሌሎች ክልሎችን ልዩ ኃይል በትነን የእኛን በሰበቡ አቆይተን ከክልሎች ሊመጣ የሚችልን ወታደራዊ ጥቃት እንመክት የምትል ብልሐት ተወልዳለች።

ሌሎች ክልሎች "የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ካልፈረሰ አናፈርስም"፡ ቀድሞ ወደክልሉ በደንብ መሣሪያ ተጭኗል። ለመደበኛውም ለኢ-መደበኛውም ነው ታዲያ!!

[ በነገራችን ላይ የደቡብ ኤሊት ከዚህ በኋላ የኦነጋውያን ዱላ ሆኖ ይቀጥላል። ዱላ ሚናው መምቻ እና መመከቻ ነው። ሬድዋን የሚባለው የኢኽዋን-ሰለፊያ ፊታውራሪ፡ በቀደም ሲለፈልፍ የነበረው የመምቻና መመከቻ ዱላነት ሚናውን ሲወጣ ነው። ኢሕአዴግም ለዚሁ ተጠቅሞት ነበር። አሁን ተሾመ ቶጋ ደግሞ የክልሎችን ኃይል የመበተን ሚና ተቀብሎ መጥቷል።]

እናም፥ ⁽⁽የኦሮሞን ስልጣን ለማስጠበቅ እና ለማጠናከር⁾⁾ በሚል የሚደረገው ሁሉ ትራጂክ ኮሜዲነቱ ከፍተኛ ነው።

በሰዎች አእምሮ እና ልብ ውስጥ የፈረሰን ስርዓት ፣ ቤት በማፍረስ ማስጠበቅ አይገርምህም!?
ከሰዎች ልብ የወጣን ስርዓት ወጣቶችን ከስራ በማሳደድ ፣ አፍኖ በማሠር፣ በጅምላ መንገድ በመዝጋት፣ ክልሎች መርጠህ የልዩ ኃይል በማፍረስ እና መሣሪያ በማስፈታት ለመጠበቅ መመኘት አይገርምህም!?

ወያኔ ሸዋ ሮቢት የመጣው 240 ታንክ በነበረው ወቅት እንዳልነበር ከመቼው ዘነጉት!? ወያኔ በቂ ትጥቅ የተሸከመው ወልድያ መጥቶ መሆኑን እያወቁ ከመቼው ዘነጉት።
ጦር መሣሪያ፤ የቆረጠን ልብ እና የከፋውን ትውልድ እንደማያስቆም፣ የቆረጠ ወጣት ስናይፐር ፊት ሲቆም እንዴት እረሱትና እዚህ ተደረሰ? ... የሚሉ መጠይቆችን እያነሳህ የመጋቢት ውርሶች ያደረሱትን ክፋት የምታስብበት ቀን አድርገው።

#መጋቢት24_ግንቦት20_መስከረም2
#የመጋቢትግፎች
#አማራያሸንፋል
#አማራ
385 viewsedited  02:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ