Get Mystery Box with random crypto!

(ብንያም ወጋየሁ) የደግ ቅናት .. . ታውቂያለሽ የኛን ነገር ሳስብ ሌሎችን | ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

(ብንያም ወጋየሁ)
የደግ ቅናት
..
.
ታውቂያለሽ
የኛን ነገር ሳስብ ሌሎችን አያለው
በሌሎች ቀናለው
ማን ነበረን እስኪ ከኛ ውጪ መቅድም?
ማለት ለምንድነው
አንቺን ለኔ አድርጎ ከፈጠረሽ ኋላ ፈጣሪ አይፈቅድም
ባይገባሽ ነው እንጂ
ፈጣሪ አይፈቅድም ብለሽ ያማረርሽው
ምን ያደርጋል መፍቀድ
እሱ እሺ ብሎ አንቺ እንቢ ካልሽው
ሰው የሚሉት ፍጡር ፍቅርን የገፋ ለት
ፍቅርን ገፋ ማለት
ኢ-ምንት አልቦ አድርገኝ ብሎ መግባት ስለት
ማነው የተሳለው?
ከሰውነት ገደብ እንነቀል ያለው
ለዚህ ነው
የምቀናው ባንቺ ስትመጪ ስትሄጂ
አይምሰልሽ ሐራም ቀና ቅናት እንጂ
አዎን እቀናለው
ያልቀኑበት ነገር አልቦነት ስላለው
ባንቺ...ቀንቻለው

ለካ በህይወት ውስጥ ሲ'ኖር በዚህ አለም
የኛን የሚያይልን ሌላ ዳኛ የለም።
(መቅናት ክፉ አይደለም)
@yotorr