Get Mystery Box with random crypto!

ተስፋሽን ፈራሁት (በድሉ ዋቅጅራ) የደጅሽ አበባ፣ እምቡጥ ሲይዝልሽ፤ የታቀፍሽው ህጻን፣ ጠብቶ ሲ | ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

ተስፋሽን ፈራሁት (በድሉ ዋቅጅራ)

የደጅሽ አበባ፣ እምቡጥ ሲይዝልሽ፤
የታቀፍሽው ህጻን፣ ጠብቶ ሲያገሳልሽ፤
ደስታሽን አይቼ፤
ተስፋሽን ቃኝቼ፤
. . . . . .ነገሽን ፈራሁት፡፡

እምቡጥ የሚያመክን፣
አመዳይ
ትላትል
ተምች በሞላበት፤
እንቡጥ የሚቀጥፍ፣
ሰው በሚኖርበት፤
. . . . . . . . . በእኔና አንቺ አለም፤
ማንቦጥ መታጨት ነው፣
መውለድ መከተብ ነው፣
የዘላለም ሀዘን፣ የዘላለም ህመም፡፡
-------------
(የተስፋ ክትባት )
@kene_tobeya