Get Mystery Box with random crypto!

'ያላለቀ ግጥም' (ቢኒያም ወጋየሁ) . . ታስታውሺው እንደው ያኔ አብረን ሳለን አለም ሁሉ ሰፍቶ | ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

"ያላለቀ ግጥም"
(ቢኒያም ወጋየሁ)
.
.
ታስታውሺው እንደው
ያኔ አብረን ሳለን
አለም ሁሉ ሰፍቶን
ሀገር ሁሉ ደልቶን
ከመፋቀር ባህር እንደተቀመጥን
የሆነ ጊዜ ላይ
ከእግረ ሙቅ ተላቀን ከፍቅር ያመለጥን
... ነበርን...
በሰራውት አለም በሰራሽው አለም
ለኛ የማይበቃ አንዳች ተዐምር የለም
(ይኸው ለኔና አንቺ ተዐምር ብርቅ አይደለም)
አንቺን የማጣቴ እልፍ ቀን ቢመጣም
ዛሬም ከአንደበቴ
ተለየሺኝ የሚል አንዳች ቃል አልወጣም
ብትሄጂም ብትርቂም
መንገድን ብታውቂም
ብትራመጂኝም
... አልተለየሺኝም...
እውነት ነው
እልፍ ተዐምር አለ አብረን የሰራነው
እውነት ነው
እልፍ ታሪክ አለ ስንቀምር የኖርነው
እልፍ ቀኖች አሉ እኛን የሚገሉን
እኛን የሚያኖሩን እልፍ"እልፎች"አሉን
... አልተለየሺኝም...
እኔ ጋር ልጅ አለሽ ብሶት የወለደው
እኔ ጋር "እኔ" አለሽ ፍቅር የገመደው.....
@yotorr