Get Mystery Box with random crypto!

#እስኪ_እናስብ hafi nge በድጋሚ አንድ የ 24 አመት ወጣት ከሚጓዝበት ባቡር አሻግሮ በ | ኢትዮ_ቅኔ&ቀልድ

#እስኪ_እናስብ hafi nge በድጋሚ

አንድ የ 24 አመት ወጣት ከሚጓዝበት ባቡር አሻግሮ በሚያያቸዉ ነገሮች ተገርሟል፡፡ ከዛም ጮክ ብሎ "አባቴ ፥ ዛፎቹን እያቸዉማ ወደኀላ እየሆዱኮ ነዉ! " ሲለዉ አባትየዉ #ፈገግ አለ ፤ በቅርብ ያሉ ተሳፋሪዋች ግን የ 24 አመት ወጣቱን በሀዘን ስሜት እንደ ልጅና #ህመምተኛ ተመለከቱት፡፡
ወጣቱ በድንገት በመደነቅ ደግሞ "አባቴ ፥ ተመልከት ደመናዉ እኮ አብሮን እየሄደ ነዉ!" አለዉ፡፡ አባትየዉ አሁንም ልጁን #በፈገግታ ተመለከተዉ ፤ በቅርብ ያለ አንድ ሰዉዬ ግን ወጣቱ በሚያሳየዉ የልጅ ፀባይ አላስችል ብሎት በንዴት ...
"ለምን ልጅህን ወደ ጥሩ የአዕምሮ ሆስፒታል አትወስደዉም?" አለዉ ለወጣቱ አባት፡፡
አባትየዉ በአንዴ ፊቱ በሀዘን ተሞላ ፣ አይኖቹ እንባ እየተናነቀዉ በእርጋታ እንዲህ ብሎ መለሰለት..."ሆስፒታል ወስጄዋለሁ... ፥ አሁን ራሱ ከዛ እየተመለስን ነዉ ፥ ልጄ ከልጅነቱ ጀምሮ ማየት አይችልም ነበር ለወራት ከታከመ በኀላ ዛሬ ነዉ ታክሞ አይቶ ከሆስፒታል የወጣዉ" አለዉ ፡፡

#

በዚህ ምድር እያንዳንዱ ሰዉ የራሱ የሆነ ታሪክ አለዉ፡፡ የሰዉን ታረክ ሳናዉቅ ሰዉ ላይ ለመፍረድ አንቸኩል፡፡ ምክንያቱም እዉነታዉን ስንሰማና ስናዉቅ ሁሌ የተናገርነው ይቆጨናልና፡፡

#የሳምንት_ሰዉ_ይበለን
#ለሰዋች_የደስታ_ምንጭ_መሆን_ባንችል_የሀዘን_ምክንያት_አንሁን
#ፈጣሪ_ሀገራችንን_ይጠብቅልን_ሰላም_ያርግልን

ሀሳባችሁን በ @hafizy_25 አድርሱን
.
ቻናሉን ከወደዳችሁት ፤ አዲስ ሰለሆነ ሼር በማረግ እንድትተባበሩን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።
@hafila25 @hafila25 @hafila25