Get Mystery Box with random crypto!

በ @tikvahethmagazine በኩል እነዚህ መረጃዎችን ከነምንጮቻቸው አሰባስበንላችሁ አስቀምጠና | etv zena

በ @tikvahethmagazine በኩል እነዚህ መረጃዎችን ከነምንጮቻቸው አሰባስበንላችሁ አስቀምጠናል ፦

- በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ለ29 ዓመታት ለተጠለሉ የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መንግሥት ምሕረት አድርጎላቸው ቀሪ ሕይወታቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲያሳልፉ ባልደረቦቻቸው በደብዳቤ ጥያቄ አቀርበዋል።

- የዎላይታ የቀድሞ ክብር ተሰናባች መካላከያ ሰራዊት አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማደረጋቸው ተገልጿል።

- የመቐለ ዩኒቨርሲቲ (ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4) ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች የመጡና ትምህርታቸው በሬድዮ መከታተል ለማይችሉ ተማሬዎች የሬድዮ ሬሲቨሮችና የእጅ ስልኮችን አበርክቷል።

- የጋሞ ሕዝብ በስነ-ልቦና ከሚቀራረባቸው ህዝቦች ጋር አደረጃጀት መፍጠር ካልቻለ ህገ-መንግስታዊ መብቱን ተጠቅሞ የራሱን ክልል የመመስረት ጥያቄውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጋሞ ዞን አስተዳደር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

- የሲዳማ ህዝብ ልዩ ምልክት የሆነውን 'የሻፌታ ታወር' ግንባታ ስምምነት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል፡፡

- የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የነበሩት እና ምርጫ ያሸነፉት ላዛረስ ቻኩዌራ አዲሱ የማላዊ ፕሬዚዳንት በመሆን ዛሬ ቃለ መሃላ መፈጸማቸው ተገልጿል።