Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዝዳንት ዩዋን ኦርላዶን ሄርናንዴዝ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ! (በአል አይን - AlAin) የሁን | etv zena

ፕሬዝዳንት ዩዋን ኦርላዶን ሄርናንዴዝ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!

(በአል አይን - AlAin)

የሁንዱራሱ ፕሬዝዳንት ዩዋን ኦርላንዶን ሄርናንዴዝ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተይዘው ሆስፒታል እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ቅዳሜ ዕለት ዶክዩመቶችን እያነበቡ የሚያሳዩ ሁለት ፎቶዎችን በትዊተር ገጻቸው “አሁንም ድረስ ሆስፒታል ውስጥ ነኝ ፤ ነገር ግን ሕዝቤን ለማገልገል ሁልጊዜም እሰራለሁ” ከሚል ጽሁፍ ጋር አስፍረዋል፡፡

በሆስፒታል ሆነው የተለያዩ ህግና ደንቦችን መፈረማቸውንም ፕሬዝዳንት ሄርናንዴዝ ገልጸዋል፡፡

አንድ የመንግስት ቃል አቀባይ ፕሬዝዳንቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና መሻሻል እያሳዩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሲኤንኤን እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው እ.ኤ.አ. ሰኔ 16 ሲሆን ባለቤታቸው እና ሁለት ረዳቶቻቸውም ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።