Get Mystery Box with random crypto!

የሃይድሮክሲክሎሮከዊን እጥረት እያጋጠመ ነው! ሃይድሮክሲክሎሮከዊን የተባለው መድኃኒትን ለኮሮና ቫ | etv zena

የሃይድሮክሲክሎሮከዊን እጥረት እያጋጠመ ነው!

ሃይድሮክሲክሎሮከዊን የተባለው መድኃኒትን ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮ እና የአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ሲቀሰቅሱ እንደነበረ አይዘነጋም።

በዚህም ሳቢያ ሃይድሮክሲክሎሮከዊን መድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ በአቅርቦት ላይ እጥረት ማስከተሉንና የዋጋ ጭማሪ መፈጠሩን #BBC ዘግቧል።

ይህ ሁኔታ ሃይድሮክሲክሎሮከዊን ለተለያዩ ህክምናዎች በሚወስዱ ህሙማን ላይ ቀጥተኛ ጫናን ማስከተሉ BBC አስነብቧል።

በቅርቡ የተደረገ ሙከራ መድኃኒቱ ኮቪድ-19 ለማከም አስተዋጽኦ እንደሌለው ቢያመለክትም ፤ አንዳንድ አገራት ግን መድኃኒቱ ጥቅም እንዳለው ማስተዋወቃቸውን ቀጥለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅትም ሃይድሮክሲክሎሮከዊን ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚፈይደው ነገር የለም በማለት በመድኃኒቱ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ሙከራ ማቆሙን ባለፈው ሳምንት አስታውቋል።