Get Mystery Box with random crypto!

#ScholarshipProgram ካስ ኢትዮጵያ/አፍሪካ ሕብረት ቢሮ የነፃ ትምሕርት ዕድል ለኢትዮጵ | ETV.News

#ScholarshipProgram

ካስ ኢትዮጵያ/አፍሪካ ሕብረት ቢሮ የነፃ ትምሕርት ዕድል ለኢትዮጵያዊያን የማስተርስ እና የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችና ምሩቃን ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ ቤተሰቦች በላከው መረጃ ገልጿል።

የማስተርስ ትምህርታችሁን በሀገር ውስጥ የጀመራችሁ እንዲሁም ለመጀመር እቅድ ያላችሁ የዚህ ስኮላርሽፕ ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ።

በተጨማሪም የማስተርስ ድግሪ ወይም PHD ኖሯችሁ ተጨማሪ ኮርሶችን መማር ለምትፈልጉ በተመሳሳይ እድሉን እንድትጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

የማመልከቻ ቀን ከነሐሴ 26/2014  - መስከረም 20/2015 ዓ/ም ነው።

ዝርዝር መስፈርቶችንና የማመልከቻ መንገዶችን https://www.kas.de/en/web/aethiopien/sur-place-scholarship-program መመልከት ይቻላል።

መልካም ዕድል!

Via @tikvahethmagazine