Get Mystery Box with random crypto!

#Update #ደቡብ_ወሎ በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን | ETV.News

#Update

#ደቡብ_ወሎ

በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው የደቡብ ወሎ ዞን ከሰሜን ወሎ ዞን ጋር በመሆን መመለስ ያለባቸውን ተፈናቃዮች እና ሰሌዳ አልባ ተሽከርካሪዎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

#አምባሰል_ወረዳ

በአምባሳል ወረዳ ሀሰተኛ አሉባልታ ሲነዙ እና ህብረተሰቡን በማወክ ዘረፋ ሊፈፅሙ ተዘጋጅተው የነበሩ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

መላው ነዋሪ በሀሰተኛ ወሬና አሉባልታ ሳይደናገጥ በፍፁም መረጋጋት አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቦለታል።

#ሐይቅ

በሐይቅ ከተማ " ከዚህ ቀደም ህወሓት ቀብሮት የነበረ ከባድ እና ቀላል መሳሪያ ተገኘ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አሳውቋል።

የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክና አካባቢው እንዳይረጋጋ እንዲሁም ተከታይ ለማብዛት ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

" ምንም ባላያችሁበትና ባላረጋገጣችሁበት አዲስ አበባ ቁጭ ብላችሁ በሀሰተኛ መረጃ ህዝብ የምትረብሹ ኃላፊነት የጎደላችሁ የማህበራዊ አንቂ ነን የምትሉ ግለሰቦች፣ ዩትዩበሮች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " ያለው የሐይቅ ፖሊስ ይህን የፈፀሙት ላይ በህግ እንዲጠየቁ እየሰራው ነው ብሏል።

ነዋሪዎች በሀሰተኛ መረጃ ይስደናገጡ በተረጋጋ ሁኔታ የአካባቢውን ሰላም በንቃት እንዲጠብቁ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia