Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ ጉዳዮች ፦ - የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ አፋር፣ | ETV.News

ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

- የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ አፋር፣አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች እስር፣ የነዳጅ ዘረፋና ተሸከርካሪ በኃይል የመውሰድ ጨምሮ ተቀባይነት የሌለው ጣልቃ ገብነት እየደረሰባቸው ነው ብለዋል። ዕርዳታ ለተቸገሩት ይደርስ ዘንድ ሁሉም ወገኖች የሰብአዊ ተግባራትን እንዲያከብሩ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል። ፓወር በዚህ መልዕክታቸው የድርጊቶቹ ፈፃሚዎችን በግልፅ አልተናግሩም። ፓወር ከዚህ ቀደም ህወሓት 150 ሺህ ጋሎን ነዳጅ ከመቐለ WFP መጋዘን መዝረፉንና ሰራተኞችን ማንገላታቱን በመግለፅ ነዳጁን እንዲመልስ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ መልዕክታቸው በአማራ እና አፋር ክልሎች ውስጥ ስለተፈፀሙ ድርጊቶችና ፈፃሚዎች በግልፅ ሳያብራሩ አልፈዋል።

- አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን በኩል የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት በእጥፍ እንዲያጠናክሩ ጠይቃለች። ጦርነቱ እንደገና መቀስቀሱ ​ና በዚህ ሳቢያ አደጋ ላይ የሚወድቀው ህይወት ያሳስበናል ብላለች።

- የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት የትግራይ ኃይሎች በአስቸኳይ ከአማራ ክልል ግጭት አቁመው ወደ ትግራይ እንዲመለሱ የኤርትራ ኃይሎችም ከትግራይ እንዲወጡ ጠይቋል። ንግግር ቢጀመር ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚቻል ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀምር እንዲያደርግ ህወሓት ከWFP የወሰደውን ነዳጅ ለሰብዓዊ ስራ እንዲውል እንዲያደርግ ጠይቋል። ይህን ግጭት ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ግጭት በማቆም ወደፖለቲካ ድርድር ማምራት ነው ብሏል ለዚህም የUK መንግስት የአፍሪካ ህብረትን የማሸማገል ጥረት እንደሚደግፍ አረጋግጧል።

@tikvahethiopia