Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ ጉዳዮች ፦ 1. ዛሬ ህወሓት የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ሆነው በ4 አቅጣጫ ጥቃ | ETV.News

ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

1. ዛሬ ህወሓት የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ሆነው በ4 አቅጣጫ ጥቃት ከፍተዋል ሲል ከሷል። ጥቃቱ ከፍቅያ ገብረ እስከ አደመይቲ፣ ከሰላሞ - ሽራሮ፣ ከጎቦ ፅንዓት ወደ እርዲ ማቲዎስና አዲ አሰር እና አዲ ጎሹ በከባድ መሳሪያ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው ብሏል። እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግስት ሆነ ከኤርትራ በኩል ለዚህ ክስ ቀጥተኛ ምላሽ አልተሰጠም።

2. የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ፦

• ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሏል ብሏል። ህወሓት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰውና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው ብሏል። ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ መውደቁን ገልጿል።

• በሕወሓት ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም ለሰላማዊ  አማራጭ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባቡለበት ሁኔታ ሕወሓትን መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ ስለሆነ ተቀባይነት የላቸውም ብሏል።

• ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገርን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይል በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል ብሏል።

3. የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በሕወሓት ላይ የትኛውንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ዛሬ ለአምባሳደሮች፣ የሚሲዮን መሪዎችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በሰጡት ማብራሪያ ገልጽዋል። ከሚወሰደው እርምጃ ጎን ለጎን አሁንም #የሰላም በሮች ክፍት መሆናቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia