Get Mystery Box with random crypto!

#Update የኢፌዴሪ መንግስት ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር (አማራ ክልል | ETV.News

#Update

የኢፌዴሪ መንግስት ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር (አማራ ክልል) አካባቢ ወረራ ከፍቷል ሲል አሳወቀ።

ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ ያወጣው የኢፌዴሪ መንግስት ፤  " ሕወሐት በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም " ብሏል።

በዚህ ምክንያት ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ነው ብሏል።

ህወሓት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ መክፈቱን የገለፀው የኢፌዴሪ መንግስት ወራራውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ ይገኛል ብሏል።

ዛሬም ድረስ ለሰላም አማራጮች የተዘረጉ እጆች አልታጠፉም ያለው የኢፌዴሪ መንግስት ይህ ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን ያድርግ ሲል አሳስቧል።

" ወገን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሓት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ ያውጣ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

(የኢፌዴሪ መንግስት መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia