Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ሕወሓት የአማራን ሕዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍ የሚያደርገው የሴራ እንቅስቃሴ ቀቢጸ ተስፋ ነው | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

አሸባሪው ሕወሓት የአማራን ሕዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍ የሚያደርገው የሴራ እንቅስቃሴ ቀቢጸ ተስፋ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
ከአማራ ሕዝብ ሂሳብ አወራርዳለሁ ያለው የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ዛሬ ላይ ደግሞ የአማራን ሕዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ የሚያደርገው የሴራ እንቅስቃሴ ቀቢጸ ተስፋ መሆኑን በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፖሊሲ ጥናት ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገለጹ።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አንተነህ ሙሉ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው ሕወሓት አማራ ክልል አካባቢ ያሉ የፖለቲካ ሁነቶችን በራሱ ዓላማ ለመጠምዘዝና ወደ ራሱ ሁኔታ ውስጥ ለመውሰድ የሚፈልግባቸው አማራጮችን እየሳየ ነው። ቡድኑ ሕዝቡ ከእሱ ጋር እንዲሰለፍና በራሱ መንገድ እንዲሄድ የሚያደርጋቸውን ጥረቶችም እያሳየ ይገኛል። ይህ ቀቢጸ ተስፋና የትም የማያደርሰው ሴራ ነው።
እንደ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገለጻ፤ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በሕዝብ ላይ እያደረሰ የነበረው ግፍ የሚታወቅ ነው።
አሁንም ጦርነት እያካሄደ ባለባቸው አካባቢዎች ተመሳሳይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል። ለሕዝብ አዛኝ ያልሆነ ቡድን ሕዝብን የትግል አጋር ለማድረግ መሞከሩ ተስፋ የለሽ ያደርገዋል።
ከዚህ ቀደም ከአማራ ሕዝብ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን ባሉበት አንደበት ዛሬ ደግሞ ከአማራ ጋር ጸብ የለንም ሲሉ ይደመጣል። ነገር ግን በተጨባጭ ከዚህ ቀደም በደረሱባቸው አማራና የአፋር አካባቢዎች ያደረሱት ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እጅግ ዘግናኝ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህ ቁስል ሳይሽር ሌላ ጥፋት ለመፈፀም ሦስተኛ ዙር ወረራ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=80568
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio