Get Mystery Box with random crypto!

#የማይረሱትየትህነግግፎች 7 በአሸባሪው የተደፈሩት የ85 አመቷ መነኩሴ 'አሁንማ ምንኩስናዬም | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

#የማይረሱትየትህነግግፎች 7
በአሸባሪው የተደፈሩት የ85 አመቷ መነኩሴ
"አሁንማ ምንኩስናዬም ፈረሰ፤ አረከሰኝ”
በትህነግ ታጣቂ የተደፈሩት የ85 አመቷ የሸዋሮቢቷ መነኩሴ ለኢፕድ የተናገሩት።
በአማራ ክልል ሸዋሮቢት ከተማ የቀበሌ 02 ነዋሪ የሆኑት እማሆይ በላይነሽ (ስማቸው የተቀየረ) 10 ልጆችን ወልደው የሳሙ የ85 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ መነኩሲት ናቸው።
በወቅቱ ላነጋገሯቸው የኢፕድ ዘጋቢዎች እንደተናገሩት፤ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ከተማዋን ተቆጣጥረው በነበረበት ወቅት የእለት ጸሎታቸውን አድርሰው ሰላም አሳድረኝ ብለው በተኙበት እኩለ ሌሊት በእነዚህ ታጣቂዎች ተደፍረዋል።
“...ያ ሰው መሳይ አውሬ አርክሶኝ ሄደ፤ በማግስቱ ሙሉ ቀን ከማህጸኔ ደም ሲፈሰኝ ዋለ። አካላቴ ሁሉ ደቋል፤ የሰውነቴ ህመም አሁንም ድረስ አለ" ያሉት እማሆይ በላይነሽ፤ ወገባቸውን እንደሚያማቸው፣ ሽንታቸውን ሲሸኑ ፊኛቸውና ማህጸናቸው አካባቢ ህመም እንደሚሰማቸው ገልጸውልናል።
ቆመው ለመራመድ መቸገራቸውንና በሰው ድጋፍ እንደሚንቀሳቀሱም ዘጋቢዎቻችን በወቅቱ ተመልክተዋል።
ዛሬም ይህ የሽብር ቡድን ከመንግሥት የተሰጠውን የሠላም ውይይት ወደ ጎን ትቶ ለ3ኛ ጊዜ አገር የማፍረስ ዕቅድ መፈጸሚያውን ጦርነት ከፍቷል። ለዳግም ዝርፊያ፣ ግድያ ብሎም አገር የማፈረስ ውጥኑን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችን ጋር ተባብሮ ጦርነት የከፈተው ትህነግ፤ "የአማራ እና አፋር ህዝብ ከጎኔ ቁሙ፤ ከእናንተ ጋር ጸብ የለኝም" ሲል የአይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ጥሪ አቅርቧል።
#የማይረሱትየትህነግግፎች -7