Get Mystery Box with random crypto!

'በባህላዊ የወርቅ ማዕድን ምርት ላይ የሚደርጉ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ሥርዓት የማስያዝ ስራ ተጠና | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

"በባህላዊ የወርቅ ማዕድን ምርት ላይ የሚደርጉ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ሥርዓት የማስያዝ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል" - የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በባህላዊ የወርቅ ማዕድን ምርት ላይ የተሰማሩትን የአከባቢ ወጣቶችም ይሁን ከውጭ ዜጎች ጋር በመመሳጠር የሚደርጉ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ሥርዓት የማስያዝ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ( አሶሳ )፣ በኦሮሚያ ( ሻኪሶ) ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ( ቤሮ), እና በጋምቤላ ( ዲማ) ወረዳ በህጋዊ መንገድ እየሰሩ ያሉትን ኩባንያዎች እና ባህላዊ የወርቅ አምራቾች ይበረታታሉ ።
ህገወጦችን በህግ ቁጥጥር ስር እያዋልን እንገኛለን ነው ያሉት ሚኒስትሩ በምንም መስፈርት ህገወጦችን አንታገስም፤ እርምጃ መውሰዳችን ይቀጥላል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio