Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ህወሓት በወልቃይት ግንባር በከፈተው ማጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

አሸባሪው ህወሓት በወልቃይት ግንባር በከፈተው ማጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ተናገሩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በሙሉ አቅሙ ቆርጦ የተነሳው የሽብርተኛው ህወሓት ሀይል በወልቃይት ግንባር በከፈተው ማጥቃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የሽብር ቡድኑ ምርኮኞች ተናገሩ።
አሸባሪው ህወሓት ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን ወልቃይትና ራያን አስመልሰን ታላቋ ትግራይን እንመሰርታለን ብሎ ጦርነት ቢያስገባንም ሳናሳካ ሙት ፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ለመሆን መገደዳቸውን ምርኮኞቹ ተናግረዋል።
የሽብር ኃይሉ የትግራይ ወጣቶችና ታዳጊዎችን በየግንባሩ ለጦርነት በመማገድ ላይ እንደሚገኝም ምርኮኞቹ መናገራቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio