Get Mystery Box with random crypto!

#የማይረሱትየትህነግግፎች 6 ሁለቱ የአፋር ወንድማማቾች አሸባሪው ትህነግ አፋር ክልል በፈጸመ | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

#የማይረሱትየትህነግግፎች 6
ሁለቱ የአፋር ወንድማማቾች
አሸባሪው ትህነግ አፋር ክልል በፈጸመው ወረራ በህጻናትና ሴቶች ላይ ያደረሰው ግድያና አስገድዶ መድፈር መቼም የሚዘነጋ አይደለም። ይህ አሸባሪ ቡድን በሁለተኛ ዙር ወረራው በአፋር ክልል የፈጸመውን ወንጀል ለመመልከት በሥፍራው ያቀኑት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል ተገኝተው ነበር። በወቅቱ በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ሁለት ወንድማማቾችን አግኝተው አነጋግረውም ነብረ።
ህጻናቱ ጣሂር ደርሳ እና ኑር ደርሳ ይባላሉ፡፡ የ 8 እና የ10 አመት ልጆች ሲሆኑ፤ የአብአላ ወረዳ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ይህ የሽብር ቡድን የህጻናቱን መንደር በከባድ መሳሪያ ሲደበድብ የሁለቱ ወንድማማቾች መኖሪያ ቤትም ከጥቃቱ አላመለጠም። በዚህም በርካቶች ሲሞቱ እነዚህ ምንም የማያወቁ ሁለት ህጻናት በዚህ መልኩ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይህ አሸባሪ ቡድን ዛሬ ሶስተኛውን ዙር ወረራ አፋር ላይ ፈጽሞ ሲያበቃ "ከህዝቡ ጋር ትናንትም ዛሬም ችግር የለብንም” ሲል ተደምጧል። ያለጦርነት መኖር የማይችለው ትህነገ ግን አሁንም በተመሳሳይ በአፋር ህዝብ ላይ ተመሳሳይ ወንገሎችን እየፈጸመ ይገኛል።
#የማይረሱትየትህነግግፎች -6