Get Mystery Box with random crypto!

በዓለም ባንክ የሚደገፉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የምከክር መድረክ ተካሄደ ** | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

በዓለም ባንክ የሚደገፉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የምከክር መድረክ ተካሄደ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የዓለም ባንክ ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ውይይቱ በዓለም ባንክ የሚደገፉ የከተማና መሠረተ ልማት ሥራዎች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥን ዓላማው ያደረገ ነው፡፡
በዓለም ባንክ ከሚደገፉ ፕሮጀክቶች መካከል በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የመኖራቸውን ያህል በጸጥታና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ መጓተቶች ሊታረሙ እንደሚገባቸውም ተጠቁሟል።
ለዚህ ተፈጻሚነት የሚመለከታቸው አካላት የየድርሻቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጸዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርና ከዋናው መ/ቤት በዓለም ባንክ የሚደገፉ ፕሮጀክቶችን የሚመሩ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio