Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሬዳዋ ሞተር ኢንዱስትሪ ጋር ስምምነት ተፈራረመ ********* | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከሬዳዋ ሞተር ኢንዱስትሪ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ሬዳዋ ሞተር ኢንዱስትሪ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ ሬዳዋ ሞተር ኢንዱስትሪ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚነት መሸጋገሩን አስመልክቶ የተደረገ መሆኑን ተገልጿል።
ሬዳዋ ሞተር ኢንዱስትሪ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ወደ 17 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ያካሂዳል።
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ እንደገለጹት፣ ሬዳዋ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚነት የተሸጋገረ የመጀመሪያው የግል ኢንዱስትሪ በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ አለው።
ከውጭ አገር ጥገኝነት ለመላቀቅ ያግዛል፤ በአሁኑ ጊዜ አብዛኛው ነገር ከውጭ የሚገባ በመሆኑ ሉአላዊነትን አሳልፎ መስጠት በመሆኑ የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
እንደ አገር ምርትን ማሳደግ ካልተቻል ኩሩ ህዝቦች መሆን አንችልም። ሬድዋ ሞተርስ ኢንዱስትሪ የውጭ ምርትን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ ጥቅም ነው።
ኢንዱስትሪዎችን ለማሳደግና የስራ እድል ለመፍጠር የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በበኩላቸው ኢንዱስትሪው ለአገር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፣ ከሌሎች ኢንዱስትሪዎች ልዩ የሚያደርገው የራሱ የሄሊኮፕተር ማረፊያና መገጣጠሚያ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
በኢንዱስትሪው ፓርክ ውስጥ የመኪና መገጣጠሚያ፣ የኬብል፣ የታሸገ ውሃና የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርትበት ፋብሪካዎች አሉት። በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ወደ 17 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ያካሂዳል ብለዋል።
በሞገስ ፀጋዬ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ
https://twitter.com/PressEthio