Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ሕወሓት ዛሬም ለሰላማዊ ዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ስደት ምክንያት ሆኗል ************ | Ethiopian Press Agency/አማርኛ /

አሸባሪው ሕወሓት ዛሬም ለሰላማዊ ዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ስደት ምክንያት ሆኗል
*************
(ኢ ፕ ድ)
አሸባሪው ሕወሓት ከውጪ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር እና በመንግስት በኩል የተደረገውን የተናጠል ተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ጎን በመጣል እንዲሁም ለሰላም የተደረጉ ጥረቶችን ባለመቀበል ኢትዮጵያን ለመበታተን ለሦስተኛ ጊዜ በከፈተው ጦርነት አሁንም ለሰላማዊ ዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ስደት ምክንያት መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በትናንትናው ዕለት በተደረገው የተቋሙ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያን ሰላም የማይፈልገው አሸባሪው ሕወሓት መንግስት ሳይወድ በግድ ሌላ ጦርነት እንዲገባ አድርጎታል። መንግስት አሁንም ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ቡድኑ የወረረውን አካባቢ በመልቀቅ ወደ ሰላም እንዲመለስ እያደረገ ይገኛል። ችግሮችን በውይይት ብቻ እንዲፈቱ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ ጥረቱ ቀጥሏል።
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የቡድኑን አካሄድ እንዲገንዘብ፣ እንዲያወግዝና ሰላም ብቸኛው አማራጭ ሆኖ እንዲቀርብ ተገቢውን የማሳወቅ ስራ መፈጸም እንዳለባቸው አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያውያን አገራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ፊታችንን ወደ ልማት ልናዞር ይገባናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በጦርነት ውስጥ ሆኖ ዘላቂ ልማት.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=80515